Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 145:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 አንድ ትውልድ የአንተን ሥራ ለሚቀጥለው ትውልድ ያስተላልፋል፤ ድንቅ ሥራህንም ይገልጣል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ሥራህን አንዱ ትውልድ ለሌላው ትውልድ ያስተጋባል፤ ብርቱ ሥራህን ያውጃል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ትውልደ ትውልድ ሥራህን ያመሰግናሉ፥ ኃይልህንም ያወራሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ነፍ​ሳ​ቸው ትወ​ጣ​ለች፥ ወደ መሬ​ትም ይመ​ለ​ሳሉ፤ ያን​ጊዜ ምክ​ራ​ቸው ሁሉ ይጠ​ፋል።

See the chapter Copy




መዝሙር 145:4
11 Cross References  

አምላክ ሆይ! ሥልጣንህን ለሚመጣው ትውልድ፥ ኀይልህንም ለሚመጡት ሁሉ እስክገልጥና አርጅቼ እስክሸብት ድረስ እንኳ አትተወኝ።


እኔ አሁን እንደማመሰግንህ ሊያመሰግኑህ የሚችሉት ሕያዋን ብቻ ናቸው፤ አባቶች ለልጆቻቸው የአንተን ታማኝነት ይናገራሉ።


እነዚህኑ ትእዛዞች ለልጆችህ አስተምራቸው፤ በቤት ስትቀመጥም ሆነ በመንገድ ስትሄድ፥ ዕረፍት በምታደርግበትም ጊዜ ሆነ ሥራ በምትሠራበት ጊዜ ሁሉ፥ እነዚህን ትእዛዞች ዘወትር አሰላስል፤


እግዚአብሔር ‘ቃሌን ይሰሙ ዘንድ ስለምፈልግ ሕዝቡን ሰብስብ’ ባለኝ ጊዜ በሲና ተራራ ላይ በእግዚአብሔር ፊት በቆማችሁበት ቀን ‘በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለእኔ እንዲታዘዙና፥ ልጆቻቸውም እኔን መፍራትን ያውቁ ዘንድ ያስተምሩአቸው’ ያለውን አስታውሱ።


እነዚህ የፑሪም ቀኖች በየትውልዱ፥ በየቤተሰቡ፥ በየሀገሩና በየከተማው መከበር እንዳለባቸው ተወሰነ፤ እነዚህም ቀኞች ሳይከበሩ መቅረት የለባቸውም፤ ከትውልዱም መካከል መታሰቢያነታቸው መቋረጥ የለበትም።


እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ ካስተዋሉት አፍልቀው አይደለምን?


Follow us:

Advertisements


Advertisements