Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 118:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ዙሪያዬን እንደ ንብ ከበቡኝ፤ ነገር ግን እሾኽ በእሳት እንደሚቃጠል በፍጥነት ተቃጠሉ፤ በእግዚአብሔርም ኀይል ደመሰስኳቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እንደ ንብ መንጋ ከበቡኝ፤ ነገር ግን እንደሚነድድ እሾኽ ከሰሙ፤ በርግጥም በእግዚአብሔር ስም አስወግዳቸዋለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ንብ ማርን እንዲከብብ ከበቡኝ፥ እሳትም በእሾህ ውስጥ እንደሚነድድ ነደዱ፥ በጌታ ስም አጠፋኋቸው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አቤቱ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፤ ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ።

See the chapter Copy




መዝሙር 118:12
18 Cross References  

በነዚያ ኮረብታዎች ላይ የሚኖሩ አሞራውያንም መጥተው ተጋጠሙአችሁ፤ ሠራዊታቸውም እንደ ንብ መንጋ ግር ብለው መጥተው እስከ ሆርማ ድረስ አሳደዱአችሁ፤ ኮረብታማ በሆነችው በኤዶም አገርም ድል አደረጉአችሁ።


ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰ “አንተ ሰይፍ፥ ጦርና ሾተል ይዘህ መጥተህብኛል፤ እኔ ደግሞ አንተ በምትፈታተነውና በእስራኤል ሠራዊት አምላክ ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ፤


ድል በማድረግህ እልል እንላለን፤ በአምላካችንም ስም ዓርማችንን ከፍ እናደርጋለን፤ እግዚአብሔር ልመናህን ሁሉ ይፈጽምልህ።


የሞኝ ሳቅ ከድስት ሥር እንደሚንጣጣ እሾኽ ስለ ሆነ ትርጒም የሌለው ከንቱ ነገር ነው።


በችግር ቀን እግዚአብሔር ጸሎትህን ይስማ! የያዕቆብ አምላክም ስም ይጠብቅህ!


እሾኽ በእሳት ላይ ተደርጎ ከመሞቁ በፊት ፈጥነህ ጠራርገህ አጥፋቸው።


ጌታችን እግዚአብሔር ሆይ! ስምህ በዓለም ሁሉ የገነነ ነው!


ክፉዎች ግን እንደ ተጣለ እሾኽ ስለ ሆኑ ማንም በእጁ ሊዳስሳቸው አይችልም።


እናንተ ሰካራሞች! እርስ በርሱ የተያያዘ እሾኽና ድርቆሽ በእሳት ተቃጥሎ እንደሚጠፋ፥ እናንተም እንዲሁ ትጠፋላችሁ።


ዳግመኛ በወይን ቦታዬ ላይ አልቈጣም፤ የወይን ቦታዬን የሚያበላሹ ኲርንችትና እሾኽ ቢኖሩ ነቃቅዬ በእሳት በማቃጠል ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ።


እናንተ ለኖራ እንደሚቃጠሉና ለእሳት እንደሚቈረጥ እሾኽ ትሆናላችሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements