Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 103:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ትእዛዞቹን የምትፈጽሙ የሚናገረውን የምታዳምጡ፤ እናንተ ኀያላንና ብርቱዎች መላእክቱ እግዚአብሔርን አመስግኑ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እናንተ ለቃሉ የምትታዘዙ መላእክቱ፣ ትእዛዙንም የምትፈጽሙ እናንተ ኀያላን፤ እግዚአብሔርን ባርኩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ቃሉን የምትፈጽሙ መላእክቱ፥ ብርቱዎችና ኃያላን፥ የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ ሁሉ፥ ጌታን ባርኩ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ጨለ​ማን ታመ​ጣ​ለህ ሌሊ​ትም ይሆ​ናል፤ በእ​ር​ሱም የዱር አራ​ዊት ሁሉ ይወ​ጡ​በ​ታል።

See the chapter Copy




መዝሙር 103:20
14 Cross References  

ታዲያ፥ መላእክት ሁሉ የሚድኑትን ሰዎች ለማገልገል የሚላኩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የሆኑ መናፍስት አይደሉምን?


እናንተ የእርሱ መላእክት ሁሉ አመስግኑት፤ በሰማይ ያላችሁ ሠራዊቱ ሁሉ አመስግኑት።


መልአኩም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህን የምሥራች እንድነግርህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኬ መጥቻለሁ።


ለመሆኑ እኔ አባቴን ብለምን እርሱ በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ የመላእክት ሠራዊት ሊልክልኝ የማይችል ይመስልሃልን?


በዚያው ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አሦራውያን ሰፈር አልፎ አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ በማግስቱ በማለዳ ሰዎች በሚነቁበት ጊዜ ሁሉም ሞተው ተገኙ።


በዚህ ዐይነት ሰዎች የመላእክትን እንጀራ በሉ፤ እግዚአብሔር የሚፈልጉትን ምግብ ሁሉ ሰጣቸው።


መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነ፥ እንዲሁም በምድር ይሁን።


እግዚአብሔር እንደ ነጐድጓድ ያለ ድምፁን በሠራዊቱ ላይ ያሰማል፤ ሠራዊቱ ምንኛ ብዙ ነው! ትእዛዙን የሚቀበሉ ከቊጥር በላይ ናቸው፤ በእርግጥም የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ ነው፤ በጣም አስፈሪ ስለ ሆነ በዚያ ቀን ማን ችሎ ይቆማል?


እናንተ የሰማይ መላእክት ሁሉ፥ ክብርና ኀይል የእግዚአብሔር ነው በሉ።


ሱራፌል ተብለው የሚጠሩ መላእክትም በዙሪያው ነበሩ፤ እያንዳንዱ መልአክ ስድስት ክንፍ አለው፤ በሁለቱ ክንፎቹ ፊቱን ይሸፍናል፤ በሁለቱ ክንፎቹ እግሮቹን ሸፍኖ በሁለት ክንፎቹ ይበር ነበር፤


ሁሉም የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ! እርሱ አዘዘ እነርሱም ተፈጠሩ።


“ሜዶናዊው ዳርዮስ በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት እኔ እርሱን ለማገዝና ለማበረታታት በአጠገቡ ቆሜ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements