Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 103:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በኃጢአታችን መጠን አልቀጣንም፤ በበደላችንም ልክ አልከፈለንም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እንደ ኀጢአታችን አልመለሰልንም፤ እንደ በደላችንም አልከፈለንም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፥ እንደ በደላችንም አልከፈለንም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ምን​ጮ​ችን ወደ ቆላ​ዎች የሚ​ልክ፤ በተ​ራ​ሮች መካ​ከል ውኆች ያል​ፋሉ፤

See the chapter Copy




መዝሙር 103:10
8 Cross References  

የደረሰብን ችግር የክፉ ሥራችንና የበደላችን ውጤት ነው፤ ሆኖም አምላካችን የቀጣኸን ልንቀጣ ከሚገባን ያነሰ ነው፤ ከዚህም በላይ ከሞት አምልጠን በሕይወት አትርፈኸናል።


ይኸውም ሳንጠፋ የቀረነው የእግዚአብሔር ምሕረት ከቶ የማያቋርጥና ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ ነው።


ኃጢአታችንን ብትከታተል ማን ከፍርድ ሊያመልጥ ይችላል?


እንደገናም ከምሕረትህ ታላቅነት የተነሣ አልተውካቸውም፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ አምላክም ስለ ሆንክ አልደመሰስካቸውም።


የጥበብ መንገድ ብዙ ስለ ሆነ፥ ምነው ጌታ የጥበብን ምሥጢር ቢገልጥልህ! ስለዚህ እግዚአብሔር የቀጣህ፥ ከሚገባህ አሳንሶ መሆኑን ዕወቅ።


እግዚአብሔር ሆይ! ስላደረግኸው አስደናቂ ሥራ ሁሉ ሰምቼ እጅግ ፈራሁ፤ አሁንም በዘመናችን የቀድሞውን ሥራህን ደግመህ አድርግ፤ በየዘመናቱም እንዲታወቅ አድርግ፤ በምትቈጣበት ጊዜ እንኳ ምሕረትህን አታርቅ።


እርሱም በሰዎች ፊት እንዲህ ብሎ ይዘምራል፤ ‘እኔ ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ የቀናውንም ነገር አጣምሜአለሁ፤ እግዚአብሔር ግን በደሌን አልቈጠረብኝም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements