Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 101:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ታማኝነትህና ስለ ትክክለኛ ፍርድህ እዘምራለሁ፤ አዜማለሁም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ስለ ምሕረትና ስለ ፍትሕ እዘምራለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአንተ በምስጋና እቀኛለሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ስማኝ፥ ጩኸ​ቴም ወደ ፊትህ ይድ​ረስ።

See the chapter Copy




መዝሙር 101:1
14 Cross References  

እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ዘወትር እዘምራለሁ፤ እውነተኛነትህንም ለትውልድ ሁሉ እገልጣለሁ።


ስለ ደግነትህ ገናናነት ይናገራሉ፤ ስለ ጽድቅህ ኀይል ከፍ ባለ ድምፅ ይዘምራሉ።


አቤቱ አዳኜ አምላኬ ሆይ! ደም ከማፍሰስ አድነኝ፤ ስለ አዳኝነትህም የምስጋና መዝሙር እዘምራለሁ።


አምላክ ሆይ! ስለ ትክክለኛ ፍርድህ የጽዮን ሕዝብ ደስ ይላቸዋል፤ የይሁዳ ከተሞችም ሐሤት ያደርጋሉ።


እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና አስፈሪነት ተመልከቱ፤ አስፈሪነቱን የሚያሳየው በወደቁት ላይ ሲሆን ቸርነቱን የሚያሳየው ግን ለእናንተ ነው፤ ይህንንም የሚያደርገው እርሱን በማመን ጸንታችሁ ብትኖሩ ነው፤ ባትጸኑ ግን እናንተም ተቈርጣችሁ ትወድቃላችሁ።


ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህ በየማለዳው መናገር፥ ስለ ታማኝነትህ በየሌሊቱ ማውራት፥ እንዴት መልካም ነው?


እግዚአብሔር መልካም የሆነውንና ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል፤ ይኸውም ፍትሕን እንድትጠብቅ፥ ደግነትን እንድትወድ፥ ከአምላክህ ጋር በትሕትና እንድትመላለስ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements