Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 7:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከዚያም በኋላ ሴትዮዋ ወጣችና አገኘችው፤ አለባበስዋም ሴትኛ ዐዳሪ መሆኗን ያመለክት ነበር፤ ሰውንም የምታስትበት ዕቅድ ነበራት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከዚያም አንዲት ሴት ልታገኘው ወጣች፤ እንደ ዝሙት ዐዳሪ ለብሳ፣ ለማሳሳት ታጥቃ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እነሆ፥ ሴት ተገናኘችው የአምንዝራ ሴት ልብስ የለበሰች፥ ነፍሳትን ለማጥመድ የተዘጋጀች።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የምንዝር ጌጥ ያላት የጐልማሶችን ልብ እንዲሰቀል የምታደርግ ሴት ያንጊዜ ትገናኘዋለች። እርስዋ የምትበርር መዳራትንም የምትወድ ናት።

See the chapter Copy




ምሳሌ 7:10
11 Cross References  

እንዲሁም ሴቶች ጠጒርን በማሳመር ወይም በወርቅ ወይም በዕንቊ ወይም ውድ በሆነ ልብስ በማጌጥ ሳይሆን በማፈርና በትሕትና ተገቢ የሆነ የጨዋ ልብስ ይልበሱ።


ለጥፋት የተዳረግሽ ኢየሩሳሌም ሆይ! ወዮልሽ! ቀይ ልብስ የለበስሽበት ምክንያት ምንድን ነው? ጌጣጌጥ ማድረግሽና ዐይንሽንስ መኳልሽ ለምንድነው? ውሽሞችሽ ጠልተውሽ ሊገድሉሽ ስለሚፈልጉ ውበትሽን የምትንከባከቢው በከንቱ ነው።


በዚህም ጊዜ ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ደረሰ፤ ኤልዛቤልም ይህን የሆነውን ነገር ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጒርዋንም ተሠርታ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ በመስኮት አዘንብላ ቊልቊል መንገዱን ትመለከት ነበር።


አንቺ የተረሳሽ ዘማዊት በገናሽን እየደረደርሽ በከተማ ውስጥ ዙሪ! እንዲያስታውሱሽ ጣዕመ ዜማ አሰሚ፤ ብዙ መዝሙሮችንም ዘምሪ!


ኢዮራምም “ኢዩ ሆይ፥ አመጣጥህ በሰላም ነውን?” ሲል ጠየቀ። ኢዩም፦ “እናትህ ኤልዛቤል ባመጣችው አስማትና የጣዖት አምልኮ ውስጥ ተነክረን እስካለን ድረስ ምን ሰላም አለ?” ሲል መለሰለት።


እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠራቸው አራዊት ሁሉ፥ እባብ እጅግ ተንኰለኛ ነበረ፤ ስለዚህ እባብ “በአትክልቱ ቦታ ካሉት ዛፎች ሁሉ ፍሬ እንዳትበሉ በእርግጥ እግዚአብሔር አዞአችኋልን?” ሲል ሴቲቱን ጠየቃት።


እንደ ወንበዴ አድብተው ይጠብቁሃል፤ ብዙ ወንዶችን በሕጋዊ ጋብቻ ታማኝ ሆነው እንዳይኖሩ አድርገዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements