ምሳሌ 6:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ልጄ ሆይ! በዚያ ሰው ሥልጣን ሥር ሆነሃል ማለት ነው፤ ስለዚህ ከእርሱ ቊጥጥር ነጻ ለመውጣት ብትፈልግ ፈጥነህ ወደ እርሱ ሂድ፤ ዋስትናውንም እንዲያወርድልህ ለምነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ልጄ ሆይ፤ ራስህን ለማዳን ይህን አድርግ፤ በጎረቤትህ እጅ ስለ ወደቅህ፣ ሄደህ ራስህን አዋርድ፤ ጎረቤትህን አጥብቀህ ነዝንዘው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ልጄ ሆይ፥ ይህን አድርግ ራስህንም አድን፥ በጎረቤትህ እጅ ወድቀሃልና፥ ፈጥነህ ሂድ፥ ጎረቤትህንም ነዝንዘው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ልጄ ሆይ፥ እኔ የማዝዝህን አድርግ፤ ራስህንም አድን፤ ስለ ወዳጅህ በክፉዎች እጅ ወድቀሃልና፤ ሰነፍ አትሁን፥ የተዋስኸውን ወዳጅህን አነሣሣው። See the chapter |