Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 4:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እኔ የማስተምራችሁ ትምህርት መልካም ስለ ሆነ ቸል አትበሉት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በጎ ትምህርት እሰጣችኋለሁ፤ ስለዚህ ትምህርቴን አትተዉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 መልካም ትምህርትን እሰጣችኋለሁና፥ ሕጌን አትተዉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 መልካም ስጦታን እሰጣችኋለሁና፥ ሕጌን አትተዉ።

See the chapter Copy




ምሳሌ 4:2
15 Cross References  

ይህን ትምህርት ለአማኞች ብታስገነዝብ የእምነትን ቃልና የምትከተለውን መልካም ትምህርት እየተመገብክ ያደግኽ፥ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ።


ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይዝነብ፤ ንግግሬም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤ በሣር ላይ እንደ ለስላሳ ዝናብ፥ በቡቃያም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥


እውነተኛውን ትምህርት በማስተማር ለመምከርና ለተቃዋሚዎችም መልስ ለመስጠት እንዲችል በተማረው መሠረት በአስተማማኝ ቃል ይጽና።


ቃሎቼ የልቤን ቅንነት ይገልጣሉ፤ ምላሶቼም እውነቱን ይናገራሉ።


በሐሳብህ ‘ትክክለኛ ነኝ’ ትላለህ፤ ለእግዚአብሔርም ‘በፊትህ ንጹሕ ነኝ’ ትለዋለህ።


ነገር ግን አንተና ሕዝብህ እኔ የሰጠኋችሁን ሕጎችና ትእዛዞች ባትጠብቁ፥ ባዕዳን አማልክትንም ብታመልኩና፥ ብትሰግዱላቸው፥


ዳዊት ሰሎሞንንም እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ የአባትህን አምላክ እንድታውቅ፥ በሙሉ ልብና በፈቃደኛ አእምሮ እንድታገለግለው ዐደራ እልሃለሁ፤ እርሱ ሐሳባችንንና ምኞታችንን ሁሉ ያውቃል፤ ወደ እርሱ ብትቀርብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል፤ ብትተወው ግን እርሱም ለዘለዓለም ይተውሃል፤


እነርሱ ሊገድሉኝ ጥቂት ቀርቶአቸው ነበር፤ እኔ ግን ትእዛዞችህን ችላ አላልኩም።


ልጄ ሆይ! የማስተምርህን አትርሳ፤ ትእዛዞቼንም በልብህ ጠብቅ።


ኢዮናዳብ የሰጠንን ትምህርት ሁሉ ተቀብለናል፤ እኛም ሆንን ሚስቶቻችን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም የወይን ጠጅ አንጠጣም፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements