Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 26:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ወፎች ወዲያና ወዲህ ሲበርሩ ምንም ጒዳት ሊያደርሱብህ እንደማይችሉ ሁሉ ከንቱ ርግማንም ምንም ጒዳት አያመጣብህም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ክንፎቿን እንደምታርገበግብ ድንቢጥ ወይም ቱር እንደምትል ጨረባ፣ ከንቱ ርግማንም በማንም ላይ አይደርስም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ወዲያና ወዲህ እንደሚበርር ድንቢጥ ወይም ጨረባ፥ እንዲሁም ከንቱ እርግማን በማንም ላይ አይደርስም።

See the chapter Copy




ምሳሌ 26:2
10 Cross References  

ታዲያ፥ እኔ እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግመዋለሁ? እግዚአብሔር ያላወገዘውንስ እንዴት አወግዛለሁ?


እነርሱ ይረግሙኛል፤ አንተ ግን ትመርቀኛለህ፤ አሳዳጆቼን አዋርዳቸው፤ እኔን አገልጋይህን ግን ደስ አሰኘኝ።


ይህም ትእዛዝ የተሰጠበት ምክንያት እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡበት ጊዜ በጒዞ ላይ ሳሉ ሞአባውያንና ዐሞናውያን ምግብና ውሃ ስለ ከለከሉአቸው ነበር፤ ይልቁንም ይህን በማድረግ ፈንታ ለበለዓም ገንዘብ ሰጥተው የእስራኤልን ሕዝብ እንዲረግምላቸው አድርገው ነበር፤ እግዚአብሔር ግን መርገሙን ወደ በረከት ለወጠው።


ምናልባት እግዚአብሔር መከራዬን አይቶ በእርሱ ርግማን ፈንታ በረከትን ይሰጠኝ ይሆናል።”


ስለዚህም ጎልያድ ዳዊትን “በትር ይዘህ የምትመጣው እኔ ውሻ ነኝን” ካለው በኋላ በአማልክቱ ስም ረገመው።


ከቤቱ ርቆ የሚሄድ ሰው ከጎጆዋ ርቃ እንደምትበር ወፍ ተንከራታች ይሆናል።


የአርኖንን ወንዝ የሚሻገሩ የሞአብ ሴቶች ከጎጆዎቻቸው ተበታትነው ክንፎቻቸውን እያራገቡ ወዲያና ወዲህ እንደሚንከራተቱ የወፍ መንጋዎች ናቸው።


አንተ የሳኦልን መንግሥት ወሰድህ ቤተሰቡንም ሁሉ ገደልክ፤ እነሆ አሁን ደግሞ እግዚአብሔር አንተን በመቅጣት ላይ ነው፤ እግዚአብሔር መንግሥትን ለልጅህ ለአቤሴሎም አሳልፎ ሰጥቶታል፤ አንተ ነፍሰ ገዳይ! እነሆ የአንተ መጥፊያ ደርሶአል።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements