Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 17:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ክፉ ሰዎች ክፉ ነገርን ይሰማሉ፤ ሐሰተኞችም ሐሰትን ያዳምጣሉ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እኩይ ሰው ክፉ ንግግር ያዳምጣል፤ ሐሰተኛም የተንኰለኛን አንደበት በጥንቃቄ ይሰማል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ክፉ ሰው የበደለኛን ከንፈር ይሰማል፥ ሐሰተኛም ወደ ተንኰለኛ ምላስ ያደምጣል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ክፉ ሰው ከሕግ ውጭ የሆኑትን ሰዎች አንደበት ይሰማል፤ ጻድቅ ግን የሐሰት ከንፈሮችን አይመለከትም። ለሚያምን በዓለም ያለው ገንዘቡ ነው፥ ለማያምን ግን መሐለቅ የለውም፥

See the chapter Copy




ምሳሌ 17:4
10 Cross References  

ሐሰተኞች ነቢያት የዓለም ናቸው፤ የሚናገሩትም የዓለምን ነገር ነው። ዓለምም እነርሱን ይሰማቸዋል።


ሕግን የማያከብሩ ሰዎች ክፉ ሰዎችን ያመሰግናሉ፤ ሕግን የሚያከብሩ ግን ክፉዎችን ይቃወማሉ።


ነቢያትንም አፋቸውን ለማስያዝ እንዲህ ይሉአቸዋል፦ ‘ቀጥተኛ የሆነውን ነገር አትንገሩን፤ እኛ ልንሰማ የምንፈልገውን ብቻ ንገሩን፤ ለስላሳና ማረሳሻ የሆነውን ነገር አስተምሩን።


ነቢያት ነን የሚሉት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናቱ በነቢያት ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቡም ይህን ሁሉ አይቃወሙም፤ ታዲያ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ በሚደርስበት ጊዜ ምን ይበጃችሁ ይሆን?”


እግዚአብሔር ለክፉ ሰዎች አሳልፎ ሰጠኝ፤ በዐመፀኞች እጅ ላይ ጣለኝ።


ሞኝ ሰው የሚነግሩትን ሁሉ አምኖ ይቀበላል፤ ብልኆች ግን እርምጃቸውን በጥንቃቄ ይመረምራሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements