Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 9:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ደመናው በድንኳኑ ላይ ለብዙ ቀኖች ቢቈይ እንኳ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ እዚያው ይቈያሉ እንጂ አይንቀሳቀሱም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ደመናው በድንኳኑ ላይ ብዙ ቀን ቢቈይም እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቃሉ እንጂ ተነሥተው አይጓዙም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ደመናውም በማደሪያው ላይ ለብዙ ቀኖች በቈየም ጊዜ እንኳ የእስራኤል ልጆች የጌታን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ደመ​ና​ውም በድ​ን​ኳኑ ላይ ብዙ ቀን በተ​ቀ​መጠ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ይጠ​ብቁ ነበር፤ አይ​ጓ​ዙ​ምም ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ደመናውም በማደሪያው ላይ ብዙ ቀን በተቀመጠ ጊዜ የእስራኤል ልጆች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር።

See the chapter Copy




ዘኍል 9:19
7 Cross References  

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል አለው፦ “አካሄድህ እንደኔ ፈቃድ ቢሆን፥ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብታደርግ፥ በቤተ መቅደሴ የአስተዳዳሪነትን፥ በአደባባዮቼም የበላይነትን ሥልጣን እሰጥሃለሁ፤ እዚህ ከቆሙት መላእክት ጋር በእኔ ፊት መግባትና መውጣት እንድትችል ባለሟልነትን እሰጥሃለሁ።


በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚገኙ መገልገያ ዕቃዎች ኀላፊዎች ይሆናሉ። እስራኤላውያንንም በድንኳኑ ውስጥ በማገልገል ተግባራቸውን ይፈጽማሉ።


ደመናው እዚያው እስካለ ድረስ ሰፈራቸውን ለቀው አይሄዱም ነበር።


ስለዚህም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ በመፈጸም ሰባት ቀን ሙሉ ሌሊትና ቀን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ትቈያላችሁ፤ ይህን ባታደርጉ ግን ትሞታላችሁ፤ ይህ እግዚአብሔር ያዘዘኝ ሕግ ነው።”


እስራኤላውያንም ከሰፈር የሚለቁትም ሆነ በሌላ ቦታ የሚሰፍሩት በእግዚአብሔር ትእዛዝ ነበር፤ ደመናው በድንኳኑ ላይ ዐርፎ እስከ አለ ድረስ በአንድ ሰፈር ይቈያሉ፤


አንዳንድ ጊዜ ደመናው በድንኳኑ ላይ የሚቈይ ለጥቂት ቀኖች ብቻ ነበር፤ ያም ሆነ ይህ በሰፈር የሚቈዩትም ሆነ ወደ ፊት የሚሄዱት በእግዚአብሔር ትእዛዝ መሠረት ነበር፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements