Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 8:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ካነጻሓቸውና ከቀደስካቸውም በኋላ ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለማገልገል ብቃት ይኖራቸዋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “ሌዋውያኑን ካነጻሓቸውና እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት አድርገህ ካቀረብሃቸው በኋላ አገልግሎታቸውን ለመፈጸም ወደ መገናኛው ድንኳን ይመጣሉ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 “ካነጻሓቸውና ለመወዝወዝም ቁርባን ካቀረብካቸው በኋላ ሌዋውያን የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ለመፈጸም ይገባሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 “ከዚ​ያም በኋላ ሌዋ​ው​ያን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ይገ​ባሉ፤ ታነ​ጻ​ቸ​ው​ማ​ለህ፤ ስጦ​ታም አድ​ር​ገህ በፊቴ ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከዚያም በኋላ ሌዋውያን የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ያገለግሉ ዘንድ ይገባሉ፤ ታነጻቸውማለህ፥ ስጦታም አድርገህ ታቀርባቸዋለህ።

See the chapter Copy




ዘኍል 8:15
9 Cross References  

ሌዋውያን ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ለእኔ ለእግዚአብሔር እንደ ልዩ ስጦታ ሆነው በመቅረብ ያገለግሉኝ ዘንድ አሮን ይቀድሳቸዋል።


“ሌዋውያንን ለእኔ የተለየ ስጦታ አድርገህ ቀድስልኝ፤ አሮንንና ልጆቹንም በእነርሱ ላይ ሹማቸው፤


“እነሆ ሌዋውያን የእኔ አገልጋዮች ናቸው፤ የግብጻውያንን በኲር ሁሉ በገደልኩ ጊዜ ከያንዳንዱ እስራኤላዊ የሚወለደውን በኲርና ከእንስሶቹም በኲር የሆነውን ሁሉ ለእኔ የተለየ እንዲሆን አድርጌ ነበር፤ አሁን ግን በኲር ሆነው የሚወለዱትን ወንዶች ልጆች የራሴ በማድረግ ፈንታ ሌዋውያንን መርጬአለሁ፤ እነርሱ የእኔ አገልጋዮች ይሆናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


ይህን ሁሉ ምግብ በአሮንና በልጆቹ እጅ ላይ አኑር፤ እርሱንም ወዝውዘው ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡት።


እኔ እነርሱን በኲር ሆነው ለሚወለዱት ለእስራኤላውያን ወንዶች ልጆች ሁሉ ምትክ አድርጌ ስለ መረጥኳቸው የእኔ ብቻ ይሆናሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements