Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 4:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በመገናኛው ድንኳን ያገለገሉትና ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው የቀዓት ቤተሰቦች ሁሉ እነዚህ ነበሩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 ይህ ከቀዓት ጐሣዎች ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ያገለገሉት ሰዎች ጠቅላላ ድምር ነው። ሙሴና አሮን፣ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እነዚህን ቈጠሯቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ጌታ በሙሴ አንደበት እንዳዘዘ፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለገሉት ሁሉ፥ ከቀዓታውያን ወገኖች የተቈጠሩት፥ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ እነዚህ ናቸው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ፥ ሙሴና አሮን እንደ ቈጠ​ሩ​አ​ቸው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ የሚ​ገ​ቡት ሁሉ፥ የቀ​ዓት ልጆች ቍጥር ይህ ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለገሉት ሁሉ፥ ከቀዓታውያን ወገኖች የተቈጠሩት፥ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ እነዚህ ናቸው።

See the chapter Copy




ዘኍል 4:37
7 Cross References  

የዓምራም፥ የይጽሃር፥ የኬብሮንና የዑዚኤል ቤተሰቦች በቀዓት ጐሣ ውስጥ ተጠቃለው ነበር፤


የተቈጠሩት ብዛታቸው ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ኀምሳ ነበር፤


በየቤተሰባቸውና በየወገናቸው የተቈጠሩት የጌርሾን ልጆች፥


እግዚአብሔር በእርሱና በእስራኤል ሕዝብ መካከል በሙሴ አማካይነት በሲና ተራራ ላይ የሰጣቸው ደንቦች፥ ሥርዓቶችና ሕጎች እነዚህ ናቸው።


ሙሴም በእግዚአብሔር ቃል እንደታዘዘው ቈጠረ።


ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉትና በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራውን ለመሥራት፥ ዕቃውን ለመሸከም የገቡት፥


በዚህም ዐይነት እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ተቈጠረ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እያንዳንዱ የማገልገልንና የመሸከምን ኀላፊነት ተቀበለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements