Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 4:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 “የቀዓትን ልጆች ከሌዋውያን ነገድ መካከል ተቀሥፈው እንዲጠፉ አታድርጉ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “የቀዓት ጐሣዎች ከሌዋውያን ተለይተው እንዳይጠፉ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 “የቀዓትን ወገኖች ነገድ ከሌዋውያን መካከል አታጥፉአቸው፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 “የቀ​ዓ​ትን ወገ​ኖች ነገድ ከሌ​ዋ​ው​ያን መካ​ከል አታ​ጥ​ፉ​አ​ቸው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የቀዓትን ወገኖች ነገድ ከሌዋውያን መካከል አታጥፉአቸው፤

See the chapter Copy




ዘኍል 4:18
13 Cross References  

በተጨማሪም እንዲህ አልኩት፦ “ሚስቶችህና ልጆችህ ሁሉ ወደ ባቢሎናውያን ይወሰዳሉ፤ አንተም በባቢሎን ንጉሥ ተይዘህ እስረኛ ትሆናለህ፤ ከእነርሱ እጅ ከቶ አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ተቃጥላ ትወድማለች።”


የታቦቱን ውስጣዊ ክፍል በመመልከታቸው እግዚአብሔር ተቈጥቶ ከቤት ሼሜሽ ሰዎች መካከል ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ እግዚአብሔርም ይህን ሁሉ እልቂት በመካከላቸው በማድረጉ የቤት ሼሜስ ሰዎች በማዘን አለቀሱ።


ቊጣዬ በእስራኤል ሕዝብ ላይ እንደገና እንዳይገለጥ በተቀደሰው ስፍራና በመሠዊያው ላይ ያለውን የአገልግሎት ኀላፊነት የምትፈጽሙት እናንተና ልጆቻችሁ ብቻ ናችሁ።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የአሮንን በትር በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት መልሰህ አኑረው፤ ዐመፀኞች የሆኑ እስራኤላውያን በእኔ ላይ ማጒረምረማቸውን ካልተዉ እንደሚሞቱ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ይቀመጥ።”


እነርሱንና ቤተሰቦቻቸውን፥ የቆሬን ተከታዮችና ያላቸውን ንብረት ሁሉ ዋጠች።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔን እግዚአብሔርን ለማየት የተወሰነውን ክልል አልፈው እንዳይመጡ ወርደህ ለሕዝቡ ንገር፤ ይህን ቢያደርጉ ግን ከእነርሱ ብዙዎቹ ይሞታሉ፤


የዓምራም፥ የይጽሃር፥ የኬብሮንና የዑዚኤል ቤተሰቦች በቀዓት ጐሣ ውስጥ ተጠቃለው ነበር፤


እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤


ወደ ተቀደሰው ስፍራ ተጠግተው እንዳይሞቱ እንዲህ አድርግላቸው፦ አሮንና ልጆቹ ወደ መቅደሱ ገብተው የያንዳንዱን ሰው ሥራና ሸክሙን ይመድቡለት።


ይህን የመሰለ ቅባት የሚሠራ ወይም ከዚህ ቅባት ወስዶ ካህን ያልሆነውን ሰው የሚቀባ ከሕዝቤ መካከል ይወገዳል።’ ”


ይህን የመሰለ ነገር ሠርቶ በመዓዛው ሊደሰት የሚፈልግ ሰው ቢኖር፥ ከሕዝቤ መካከል ይወገዳል።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements