Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 32:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21-22 የጦር ሰዎቻችሁ ሁሉ ዮርዳኖስን መሻገር፥ በእግዚአብሔር አዛዥነት በጠላቶቻችን ላይ መዝመት፥ እግዚአብሔር ድል አድርጎ፥ ምድራቸውን እስኪወስድ ድረስ መዋጋት አለባቸው፤ ይህን ካደረጋችሁ በኋላ መመለስ ትችላላችሁ፤ በዚያን ጊዜ ለእግዚአብሔርም ሆነ ለወገኖቻችሁ ለእስራኤላውያን ያለባችሁን ግዴታ ትወጣላችሁ፤ ከዚያ በኋላ ይህ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለው ምድር የእናንተ ርስት መሆኑን እግዚአብሔር ያረጋግጥላችኋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እንዲሁም ጠላቶቹን ከፊቱ አሳድዶ እስኪያስወጣ ድረስ ሁላችሁም በእግዚአብሔር ፊት ለጦርነት ዝግጁ ሆናችሁ ዮርዳኖስን ብትሻገሩ፣

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እርሱም ጠላቶቹን ከፊቱ እስኪያሳድድ ድረስ ከእናንተ ለጦርነት የተዘጋጀው ሰው ሁሉ በጌታ ፊት ዮርዳኖስን ቢሻገር፥

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እር​ሱም ጠላቱ ከፊቱ እስ​ኪ​ጠፋ ድረስ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን ይዞ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ቢሻ​ገር፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እርሱም ጠላቶቹን ከፊቱ እስኪያሳድድ ድረስ ምድሪቱም በእግዚአብሔር ፊት ድል እስክትሆን ድረስ ከእናንተ ሰው ሁሉ ጋሻ ጦሩን ይዞ በእግዚአብሔር ፊት ዮርዳኖስን ቢሻገር፥

See the chapter Copy




ዘኍል 32:21
3 Cross References  

ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ይህ የተናገራችሁት ሁሉ እውነት ከሆነ እዚህ በእግዚአብሔር ፊት ወደ ጦርነት ለመሄድ ተዘጋጁ።


“አምላካችሁ እግዚአብሔር ይህን ምድር ሰጥቶ ያሳርፋችኋል ብሎ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ቃል አስታውሱ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements