ዘኍል 32:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ከዚያም በኋላ ከወገኖቻችን ከእስራኤላውያን ጋር ወደ ጦርነት ለመሄድና የራሳቸው ወደሆነችው ምድር ገብተው እስኪሰፍሩ ድረስ በግንባር ቀደምትነት ተሰልፈን ለመዋጋት ዝግጁዎች እንሆናለን፤ እኛም ይህን ግዳጅ ፈጽመን እስከምንመለስ ልጆቻችን በእነዚህ በተመሸጉ ከተሞች ይኖራሉ፤ በዚህች ምድር ከሚኖሩትም ሰዎች ወገን ጒዳት አይደርስባቸውም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ይሁን እንጂ ወደ ስፍራቸው እስክናገባቸው ድረስ ታጥቀንና በእስራኤላውያን ፊት ግንባር ቀደም ሆነን ለመሄድ ዝግጁ ነን፤ በዚህም ጊዜ ሴቶቻችንና ልጆቻችን በምድሪቱ ላይ ካሉት ነዋሪዎች እንዲጠበቁ በተመሸጉ ከተሞች ይኖራሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 እኛ ግን ለጦርነት ተዘጋጅተን ወደ ስፍራቸው እስክናገባቸው ድረስ በእስራኤል ልጆች ፊት እንድሄዳለን፤ በዚህም ምድር ስላሉ ሰዎች ልጆቻችን በተመሸጉ ከተሞች ይቀመጣሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 እኛ ግን ለጦርነት ታጥቀን ወደ ስፍራቸው እስክናገባቸው ድረስ በእስራኤል ልጆች ፊት እንሄዳለን፤ በዚህም ምድር ስላሉ ሰዎች ልጆቻችን በተመሸጉ ከተሞች ይቀመጣሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 እኛ ግን ለጦርነት ተዘጋጅተን ወደ ስፍራቸው እስክናገባቸው ድረስ በእስራኤል ልጆች ፊት እንድሄዳለን፤ በዚህም ምድር ስላሉ ሰዎች ልጆቻችን በተመሸጉ ከተሞች ይቀመጣሉ። See the chapter |