Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 31:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ስለዚህም ሙሴ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት መባውን ለእግዚአብሔር ልዩ ስጦታ በማድረግ ለአልዓዛር ሰጠው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው የእግዚአብሔር ድርሻ የሆነውን ግብር ለካህኑ አልዓዛር ሰጠው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው ሙሴ ለጌታ የስጦታ ቁርባን የሆነውን ግብር ለካህኑ ለአልዓዛር ሰጠው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሙሴ፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለ​ዩ​ትን ግብር ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ሰጠው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ሙሴ ለእግዚአብሔር ለማንሣት ቍርባን የሆነውን ግብር ለካህኑ ለአልዓዛር ሰጠው።

See the chapter Copy




ዘኍል 31:41
14 Cross References  

“እስራኤላውያን ለእኔ የሚያቀርቡአቸውን ልዩ ስጦታዎች ሁሉ ለእናንተ፥ ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቻችሁ ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም ከእናንተና ከዘሮቻችሁ ሁሉ ጋር የምገባው የማይሻር የጨው ቃል ኪዳን ነው።”


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አሮንን እንዲህ አለው፦ “ለእኔ የሚቀርበውን የማይቃጠለውን ልዩ መባ ሁሉ ለአንተ የሰጠሁህ መሆኑን አስታውስ፤ እርሱ ለዘለዓለም ለአንተና ለዘሮችህ ሁሉ ድርሻ እንዲሆን ሰጥቻችኋለሁ፤


ቤተ ክርስቲያንን በደንብ የሚያስተዳድሩ፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙ ሽማግሌዎች እጥፍ ክብር ይገባቸዋል፤


ቃሉን የሚማር ሰው ከአስተማሪው ጋር መልካሙን ነገር ሁሉ ይካፈል።


ለሠራተኛ ምግቡ የሚገባው ስለ ሆነ ለመንገዳችሁ ከረጢት፥ ትርፍ እጀ ጠባብ፥ ትርፍ ጫማ፥ በትርም አትያዙ።


በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት ልዩ ስጦታ ሁሉ ስጦታውን ለሚቀበለው ካህን ድርሻ ይሆናል።


እያንዳንዱ ሰው ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው ልዩ ስጦታ የራሱ የሰውዬው ነው፤ ለካህኑ ከሰጠ ግን የካህኑ ይሆናል።”


ለወታደሮቹ የተሰጡት ከወንድ ጋር ግንኙነት ያላደረጉ ሴቶች ዐሥራ ስድስት ሺህ ሲሆኑ፥ ከእነዚህም ሠላሳ ሁለቱ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለዩ ነበሩ።


የማኅበሩ አባሎች ድርሻ ከወታደሮቹ ድርሻ ጋር ተመሳሳይና እኩል ነበር፤


ሄደውም በሙሴና በአሮን አማካይነት እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ሁሉ አደረጉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements