ዘኍል 30:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ሳታገባ በአባትዋ ቤት የምትኖር ልጃገረድ ወይም ያገባች ሴት ስእለት ወይም የመሐላ ቃል በምትገባበት ጊዜ የአባት ወይም የባል ኀላፊነትንና መብትን በተመለከተ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው ደንብ ይህ ነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 እነዚህ እንግዲህ በባልና በሚስት፣ በአባትና ዐብራው በቤት ውስጥ በምትኖር ልጁ መካከል ያለውን ግንኙነት አስመልክቶ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው ሥርዐቶች ናቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 እርሷ በብላቴንነትዋ ጊዜ በአባትዋ ቤት ሳለች በአባትና በልጂቱ መካከል፥ ወይም በባልና በሚስት መካከል እንዲሆን ጌታ ሙሴን ያዘዘው ሥርዓት ይህ ነው።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 እርስዋ በብላቴንነቷ ጊዜ በአባቷ ቤት ሳለች በአባትና በልጂቱ መካከል፥ ወይም በባልና በሚስት መካከል ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘው ሥርዐት ይህ ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 እርስዋ በብላቴንነትዋ ጊዜ በአባትዋ ቤት ሳለች በአባትና በልጂቱ መካከል፥ ወይም በባልና በሚስት መካከል ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘው ሥርዓት ይህ ነው። See the chapter |