Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 3:51 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

51 እግዚአብሔር ባዘዘው ቃል መሠረት ሙሴ የመዋጃውን ገንዘብ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጠ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

51 ሙሴም በእግዚአብሔር ቃል በታዘዘው መሠረት የመዋጃውን ገንዘብ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጣቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

51 ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው፥ እንደ ጌታ ቃል፥ ሙሴ የመዋጃውን ገንዘብ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጠ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

51 እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሙሴ የመ​ቤ​ዣ​ውን ገን​ዘብ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ሰጠ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

51 እንደ እግዚአብሔርም ቃል፥ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው፥ ሙሴ የመቤዣውን ገንዘብ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጠ።

See the chapter Copy




ዘኍል 3:51
11 Cross References  

ይህንንም የመዋጃ ገንዘብ ለአሮንና ለልጆቹ ስጥ።”


በዐደራ የተሰጣችሁን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ መንጋውን የምትጠብቁትም በግድ ሳይሆን እግዚአብሔር በሚፈልገው ዐይነት፥ በፈቃደኛነት ይሁን፤ ለገንዘብ በመስገብገብ ሳይሆን ለማገልገል ባላችሁ ፍላጎት ይሁን።


ሌሎች ይህን ነገር ከእናንተ የመካፈል መብት ያላቸው ከሆነ ታዲያ፥ እኛ ከዚህ የሚበልጥ መብት እንዴት አይኖረንም? እኛ ግን በዚህ መብት አልተጠቀምንም፤ ይህን ማድረጋችንም የክርስቶስ የምሥራች ቃል ከመስፋፋት እንዳይገታ በማሰብ ሁሉን ነገር ታግሠን እንቻል ብለን ነው።


እኔ የማንንም ብር፥ ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም።


“የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ይመሩበት ዘንድ በሲና ተራራ ላይ ለአገልጋዬ ለሙሴ የሰጠሁትን ሕግና ትእዛዝ አስታውሱ።


ሙሴም እጅግ ተቈጥቶ እግዚአብሔርን እንዲህ አለ፦ “እነዚህ ሰዎች የሚያቀርቡልህን መባ አትቀበል፤ እኔ ከእነርሱ አንዱን እንኳ አልበደልኩም፤ ሌላው ቀርቶ ከአህዮቻቸው አንዱን እንኳ አልወሰድኩም።”


ከእስራኤላውያን በኲሮች በመቅደሱ ሚዛን መሠረት ገንዘቡን አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሥልሳ አምስት ሰቅል ብር ወሰደ።


እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤


እስራኤላውያን ሁሉ ታዛዦች በመሆን እግዚአብሔር በሙሴና በአሮን አማካይነት ያዘዘውን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ሆኑ፤


በዚህም ዐይነት ሙሴ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በሲና በረሓ ሕዝቡን ቈጠረ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements