Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 3:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 የእነርሱም ኀላፊነት በቃል ኪዳኑ ታቦት፥ በገበታው፥ በመቅረዙ፥ በመሠዊያዎቹ፥ ካህናቱ በተቀደሰው ስፍራ በሚገለገሉባቸው ንዋያተ ቅድሳት፥ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በሚያስገባው መጋረጃ ላይ ሲሆን፥ በአጠቃላይ እነዚህን ነገሮች በሚመለከት አገልግሎት ኀላፊነቱ የእነርሱ ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 እነርሱም ታቦቱን፣ ጠረጴዛውን፣ መቅረዙን፣ መሠዊያዎቹን፣ ለመቅደሱ አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች፣ መጋረጃዎችንና ከነዚህ ጋራ ተያይዞ አገልግሎት የሚሰጠውን ሁሉ ይጠብቃሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ታቦቱንም፥ ገበታውንም፥ መቅረዙንም፥ መሠዊያዎቹንም፥ ካህናቱም የሚገለገሉባቸውን የመቅደሱን ዕቃዎች፥ መጋረጃውንም፥ መገልገያውንም ሁሉ ይጠብቃሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ታቦ​ቱ​ንም፥ ገበ​ታ​ው​ንም፥ መቅ​ረ​ዙ​ንም፥ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ት​ንም የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ፥ መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም፥ ማገ​ል​ገ​ያ​ው​ንም ሁሉ ይጠ​ብ​ቃሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ታቦቱንም፥ ገበታውንም፥ መቅረዙንም፥ መሠዊያዎቹንም፥ የሚያገለግሉበትንም የመቅደሱን ዕቃ፥ መጋረጃውንም፥ ማገልገያውንም ሁሉ ይጠብቃሉ።

See the chapter Copy




ዘኍል 3:31
15 Cross References  

የመታጠቢያውንም ሳሕን በድንኳኑና በመሠዊያው መካከል አስቀምጦ ውሃ ሞላበት።


ባጽልኤልም ከግራር እንጨት የቃል ኪዳኑን ታቦት ሠራ፤ ርዝመቱ መቶ ዐሥር ሳንቲ ሜትር፥ የጐኑ ስፋት ሥልሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር፥ ቁመቱም ሥልሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር ነበር።


ሰዎች መብራት አብርተው በቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዲያበራ በከፍተኛ ቦታ ያስቀምጡታል እንጂ ከእንቅብ በታች አያኖሩትም።


የቀዓትም ጐሣ መሪ የዑዚኤል ልጅ የሆነው ኤሊጻፋን ነበር።


የሌዋውያን ሁሉ አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ነበር፤ እርሱ በተቀደሰው ስፍራ ለሚያገለግሉት ሰዎች ሁሉ የበላይ ኀላፊ ነበር።


በዚያን ጊዜ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከሙ፥ በፊቱም በመቆም እንዲያገለግሉትና ሕዝቡን በእግዚአብሔር ስም እንዲባርኩ የሌዊን ነገድ በመለየት ሾመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የሌዊ ነገድ ትውልድ አገልግሎት ይኸው ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements