Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 21:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ከዚህም የተነሣ ባለቅኔዎች እንኳ እንዲህ እያሉ ይቀኙ ነበር፦ “ወደ ሐሴቦን ኑ! ይህች ከተማ ትገንባ! የሲሖን ከተማ ትመሥረት፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እንግዲህ ባለቅኔዎች እንደዚህ ያሉት ለዚህ ነው፤ “ወደ ሐሴቦን ኑ፣ እንደ ገና ትገንባ፤ የሴዎንም ከተማ ተመልሳ ትሠራ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ስለዚህ ባለቅኔዎች እንዲህ ብለው በምሳሌ ተቀኙ፦ “ወደ ሐሴቦን ኑ። የሴዎን ከተማ ይሠራ፥ ይመሥረትም፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ስለ​ዚህ የም​ሳሌ ሰዎች እን​ዲህ ብለው ይና​ገ​ራሉ፦ “ወደ ሐሴ​ቦን ኑ፤ የሴ​ዎን ከተማ ይመ​ሥ​ረት፤ ይገ​ንባ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ስለዚህ በምሳሌ እንዲህ ተብሎ ተነገረ፦ ወደ ሐሴቦን ኑ። የሴዎን ከተማ ይሠራ፥ ይመሥረት፤

See the chapter Copy




ዘኍል 21:27
6 Cross References  

ሰው ሁሉ እንደነዚህ ባሉት ሰዎች ላይ በመሳለቂያ እንቆቅልሽ እንዲህ ይላል፦ “ያንተ ያልሆነውን የምታግበሰብስ ወዮልህ! በመያዣነት በተወሰዱ ዕቃ ራስህን የምታበለጽገው እስከ መቼ ነው?”


በባቢሎን ንጉሥ ላይ እንዲህ እያላችሁ ታፌዙበታላችሁ፦ “እነሆ ጨቋኙ ንጉሥ ወደቀ! ከእንግዲህ ወዲህ ማንንም አይጨቊንም!


ከዚህም የተነሣ በእግዚአብሔር መሪነት ስለ ተደረገው ጦርነት በሚናገር የታሪክ መጽሐፍ እንዲህ ተብሎአል፦ “በሱፋ ክልልና በሸለቆዎች ውስጥ የሚገኘው ዋሄብ፥ የአርኖን ወንዝ፥


ሐሴቦን የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን መናገሻ ከተማ ነበረች፤ እርሱም ከሞአብ የቀድሞ ንጉሥ ጋር ተዋግቶ እስከ አርኖን ወንዝ ያለውን ምድር ሁሉ ወስዶበት ነበር።


ከሐሴቦን እሳት ወጣ፤ ነበልባልም ከሲሖን ከተማ፥ የሞአብን ዔር አጠፋ የአርኖንንም ከፍተኛ ቦታዎች ደመሰሰ።


እነሆ የቅጽሩ ግንብ ተሠርቶ አለቀ፤ የቅጽር በሮችም ሁሉ በየቦታቸው ተገጣጥመው ነበር፤ ቤተ መቅደሱን የሚጠብቁ ዘበኞች ለመዘምራን ቡድን አባላትና ለሌሎችም ሌዋውያን የሥራ ድርሻቸው ተመድቦላቸው ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements