Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 20:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ኤዶማውያን ግን እንዲህ አሉ፤ “በአገራችን አልፋችሁ እንድትሄዱ አንፈቅድላችሁም! ለመግባት ብትሞክሩ ግን በሰልፍ ወጥተን እንወጋችኋለን።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ኤዶም ግን እንዲህ ሲል መለሰ፤ “በዚህ በኩል አታልፉም፤ እናልፋለን የምትሉ ከሆነ በሰልፍ ወጥተን በሰይፍ እንመታችኋለን።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ኤዶምያስም፦ “በምድሬ ላይ አታልፍም አለበለዚያ ግን አንተን በሰይፍ ልገጥምህ እወጣለሁ” አለው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ “በእኔ በኩል አታ​ል​ፍም፤ ይህ ካል​ሆነ ግን እን​ዋ​ጋ​ለን፤ በጦ​ርም እቀ​በ​ልህ ዘንድ እወ​ጣ​ለሁ” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ኤዶምያስም፦ በሰይፍ እንዳልገጥምህ በምድሬ ላይ አታልፍም አለው።

See the chapter Copy




ዘኍል 20:18
6 Cross References  

ኤዶምን አሸንፎ የራሱ ያደርጋታል፤ ጠላቱ ሴርም የእርሱ ትሆናለች፤ እስራኤል ድል አድራጊ እንደ ሆነ ይኖራል።


የእስራኤል ሕዝብም “እኛ ከዋናው መንገድ አንወጣም፤ እኛ ወይም እንስሶቻችን ከውሃችሁ ብንጠጣ እንኳ ዋጋ እንከፍላችኋለን፤ እኛ የምንፈልገው በምድራችሁ አልፈን መሄድ ብቻ ነው” ሲሉ መለሱላቸው።


ኤዶማውያን ግን “አይሆንም! አናሳልፋችሁም!” አሉ፤ ብርቱ የጦር ሠራዊትም አሰልፈው የእስራኤልን ሕዝብ ሊወጉ ወጡ።


እስራኤላውያን በኤዶም ግዛት ዙሪያ ለመሄድ አስበው ከሖር ተራራ ተነሥተው ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ ተጓዙ፤ ነገር ግን በመንገድ ሳሉ የሕዝቡ ትዕግሥት አለቀ፤


ሲሖን ግን የእስራኤል ሕዝብ በግዛቱ አልፈው እንዲሄዱ አልፈቀደላቸውም፤ እንዲያውም ሠራዊቱን ሁሉ ሰብስቦ በበረሓ ውስጥ ወዳለችው ወደ ያሀጽ በመሄድ በእስራኤላውያን ላይ ጦርነት አደረገ።


በኤዶም የሚኖሩ የዔሳው ዘሮችና በዔር የሚኖሩ የሞአብ ዘሮች በግዛታቸው በኩል እንድናልፍ እንደ ፈቀዱልን ሁሉ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረን እግዚአብሔር ወደሚያወርሰን ምድር እስክንገባ ድረስ በዚያ ለማለፍ ፍቀድልን።’


Follow us:

Advertisements


Advertisements