Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 19:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “አንድ ሰው በድንኳኑ ውስጥ በሚሞትበት ጊዜ ተፈጻሚ የሚሆነው ሕግ ይህ ነው። እርሱ በሞተበት ጊዜ በዚያ ድንኳን ውስጥ ያለ ሰው ወይም ወደዚያ የሚገባ ሰው ለሰባት ቀን ያልነጻ ሆኖ ይቈያል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “አንድ ሰው በድንኳን ውስጥ በሚሞትበት ጊዜ የሚፈጸመው ሥርዐት የሚከተለው ነው፤ ወደ ድንኳኑ የሚገባም ሆነ በዚያ ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው እስከ ሰባት ቀን ድረስ የረከሰ ይሆናል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “ሰው በድንኳን ውስጥ ቢሞት ሕጉ ይህ ነው፤ ወደ ድንኳኑ የሚገባ ሁሉ በድንኳኑም ውስጥ ያለው ሁሉ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “ሰው በቤት ውስጥ ቢሞት ሕጉ ይህ ነው፤ ወደ ቤት የሚ​ገባ ሁሉ በቤ​ቱም ውስጥ ያለው ሁሉ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሰው በድንኳን ውስጥ ቢሞት ሕጉ ይህ ነው፤ ወደ ድንኳኑ የሚገባ ሁሉ በድንኳኑም ውስጥ ያለው ሁሉ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል።

See the chapter Copy




ዘኍል 19:14
13 Cross References  

የማናቸውም ሰው አስከሬን የአባቱም ሆነ ወይም የእናቱ ወደ አለበት ቤት ገብቶ ራሱን አያርክስ፤


ለማንጻት የተመደበው ውሃ በእርሱ ላይ ስላልፈሰሰ በድን ነክቶ ራሱን የማያነጻ፥ እንደ ረከሰ ይቈያል፤ እንዲህ ያለው ሰው ድንኳኑን ያረክሳል፤ ስለዚህም ከእስራኤል ሕዝብ ይለይ።


በድንኳኑ ውስጥ የሚገኝ ክዳን የሌለው ማንኛውም እንስራም ሆነ ማሰሮ የረከሰ ይሆናል።


“እነዚህም ለማንኛውም ተላላፊ ለሆነ የሥጋ ደዌ በሽታ፥ ለእከክ የሥርዓት መመሪያዎች ናቸው።


ከሰውነቱ ፈሳሽ ነገር ስለሚወጣበትና ስለሚያረክሰው ሰው የተሰጠ ደንብ ይህ ነው።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከሕዝቡ መካከል የሞተውን ሰው አስከሬን በመንካት ስለ ሞተ ሰው ማናቸውም ራሳቸውን እንዳያረክሱ የአሮን ተወላጆች ለሆኑ ካህናት ንገራቸው፤


“የሥጋ ደዌ በሽታ ያለበትን፥ ወይም ከሰውነቱ ፈሳሽ የሚወጣውንና ሬሳ በመንካት የረከሰውን ሰው ሁሉ ከሰፈር ያወጡ ዘንድ እስራኤላውያንን እዘዝ፤


በናዝራዊነት በአለበት ጊዜ ሁሉ ወደ ሞተ ሰው በድን አይቅረብ፤


“በድንገት አንድ ሰው በአጠገቡ ቢሞት፥ የተቀደሰውን ራሱንም ቢያረክስ፥ በሰባተኛው ቀን ራሱን ይላጭ።


ነገር ግን በድን ከመንካታቸው የተነሣ ያልነጹ ጥቂት ሰዎች ስለ ነበሩ በዚያን ቀን የፋሲካን በዓል ማክበር አልቻሉም፤ ስለዚህ እነርሱ ወደ ሙሴና አሮን ዘንድ ቀርበው እንዲህ አሉ፤


እንዲሁም ማንኛውንም ልብስ ወይም ከቈዳ፥ ከፍየል ጠጒር ወይም ከእንጨት የተሠራ ነገር ሁሉ አጽዱ።”


ከዚያም በኋላ እስራኤላውያን ያንን ሁሉ ሬሳ ቀብረው ምድሪቱን እንደገና ለማጽዳት ሰባት ወራት ይፈጅባቸዋል።


ይህን ካደረገ ግን ከነጻም በኋላ እንኳ ሰባት ቀን መቈየት አለበት፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements