Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 18:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የላም፥ የበግና የፍየል በኲር ግን መዋጀት የለባቸውም፤ እነርሱ በፍጹም የእኔ ስለ ሆኑ መሥዋዕት ሆነው መቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ አፍስሱት፤ ስባቸውንም መዓዛው እኔን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት እንዲሆን በእሳት አቃጥሉት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “የተቀደሱ ስለ ሆኑ የበሬ፣ የበግ ወይም የፍየል በኵር የሆኑትን አትዋጃቸውም፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ ትረጨዋለህ፤ ሥባቸውንም ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ ታቃጥለዋለህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ነገር ግን የላም በኵራት ወይም የበግ በኵራት ወይም የፍየል በኵራት አትዋጅም፤ የተቀደሱ ናቸው፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ እርጨው፥ ስባቸውንም ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርገህ አቃጥለው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ነገር ግን የላ​ሞ​ቹን በኵ​ራት፥ ወይም የበ​ጎ​ቹን በኵ​ራት፥ የፍ​የ​ሎ​ች​ንም በኵ​ራት አት​ቤ​ዥም፤ ቅዱ​ሳን ናቸ​ውና፤ ደማ​ቸ​ውን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ ስባ​ቸ​ው​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን መሥ​ዋ​ዕት ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ነገር ግን የላም በኵራት ወይም የበግ በኵራት ወይም የፍየል በኵራት አትቤዥም፤ የተቀደሱ ናቸው፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ ትረጨዋለህ፥ ስባቸውንም ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ለእሳት ቍርባን ታቃጥለዋለህ።

See the chapter Copy




ዘኍል 18:17
5 Cross References  

እርሱንም ዐርደህ ደሙን በመሠዊያው ጐን በአራቱም ማእዘን እርጨው፤


ካህኑ ደሙን በድንኳኑ መግቢያ በመሠዊያው ላይ ይርጭ፤ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ጣፋጭ ሽታ ይሆን ዘንድ ስቡንም ያቃጥለው፤


አንድ ወር የሞላቸው ሕፃናት በይፋ በተመደበው ዋጋ መሠረት አምስት ሰቅል ጥሬ ብር የቤዛ ዋጋ ተከፍሎላቸው ሊዋጁ ይችላሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements