Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 15:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “ምናልባት እናንተ ሆን ብላችሁ ሳይሆን ባለማወቅ እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጠው ትእዛዞች መካከል አንዱን ሳትጠብቁ ብትቀሩ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “ ‘እንግዲህ ካለማወቅ የተነሣ እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጣቸው ትእዛዞች አንዱን ሳትፈጽሙ ብትቀሩ፣ ይህም ማለት

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 “ነገር ግን ስሕተት ባለማወቅ ብትፈጽሙ፥ ጌታም ለሙሴ ያዘዛቸውን እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ባታደርጉ፥

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 “ብት​በ​ድ​ሉም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ህን ትእ​ዛ​ዛት ሁሉ ባታ​ደ​ርጉ፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ብትስቱም፥ እግዚአብሔርም ለሙሴ ያዘዛቸውን እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ባታደርጉ፥

See the chapter Copy




ዘኍል 15:22
10 Cross References  

“ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ይህ ነው፦ ማንም ሰው ተሳስቶ ኃጢአት ቢሠራ ወይም ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ትእዛዞች አንዱን ቢተላለፍ ከዚህ የሚከተለውን ሥርዓት ይጠብቅ፦


ነገር ግን የጌታውን ፈቃድ ባለማወቅ፥ ቅጣት የሚያመጣበትን ነገር አድርጎ ቢገኝ ቅጣቱ ይቀልለታል፤ ብዙ ከተሰጠው ሰው ብዙ ይፈለግበታል፤ ብዙ ዐደራም ከተሰጠው ሰው፥ ብዙ ይጠበቅበታል።”


የራሱን ስሕተት የሚያይ ማንም የለም፤ አምላኬ ሆይ! ከተሰወረ በደል አንጻኝ።


ካህኑም በዚህ ዐይነት ስለዚያ ሰው ኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕትን ያቀርባል፤ ያም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል፤ የቀረው ዱቄት የእህል መባ በሚቀርብበት ዐይነት ለካህኑ ይሁን።”


“ኃጢአት የሠራውና ባለማወቅም እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸው ትእዛዞች አንዱን የተላለፈውና በደለኛ የሆነው ሰው ከተራው ሕዝብ ወገን ከሆነ፥


“ኃጢአት የሠራውና ባለማወቅ እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ካዘዘው ትእዛዝ በመተላለፍ በደለኛ የሆነው የሕዝብ መሪ ከሆነ፥


ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ከአዲስ እህል ከምትጋግሩት ኅብስት እየተነሣ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ ሆኖ መቅረብ አለበት።


ወይም ምናልባት ወደፊት ዘሮቻችሁ በሙሴ አማካይነት ያዘዘውን ትእዛዝ ሁሉ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements