Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 14:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ሙሴ ግን እንዲህ አለ፤ “ታዲያ አሁንም ደግማችሁ ለእግዚአብሔር የማትታዘዙት ስለምንድን ነው? ያሰባችሁት አይሳካላችሁም!

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ሙሴ ግን እንዲህ አለ፤ “የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትጥሳላችሁ? ይህም አይሳካላችሁም!

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 ሙሴም እንዲህ አለ፦ “የጌታን ትእዛዝ ለምን አሁንም ትተላለፋላችሁ? ይህ አይሳካላችሁም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 ሙሴም አለ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ለምን ትተ​ላ​ለ​ፋ​ላ​ችሁ? ይህ ለእ​ና​ንተ መል​ካም አይ​ደ​ለም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 ሙሴም አለ፦ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ? አይጠቅማችሁም።

See the chapter Copy




ዘኍል 14:41
7 Cross References  

ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር መንፈስ በካህኑ በዮዳሄ ልጅ በዘካርያስ ላይ ወረደ፤ እርሱም ሕዝቡ ሊያዩት በሚችሉበት ከፍ ያለ ስፍራ ላይ ቆሞ “እግዚአብሔር ‘ትእዛዞቼን ስለምን ትተላለፋላችሁ? በገዛ ራሳችሁስ ላይ ስለምን ጥፋትን ታመጣላችሁ?’ ሲል ይጠይቃችኋል፤ እንግዲህ እናንተ ስለ ተዋችሁት እርሱም ትቶአችኋል” አላቸው።


ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ይወሰዳል፤ እኔ በሞት እስክጐበኘው ድረስ በዚያ ይኖራል፤ ከባቢሎናውያን ጋር ለመዋጋት ቢሞክር እንኳ አይሳካለትም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ በዕፍረት ከዚያ ቦታ ትሄጂአለሽ፤ እኔ እግዚአብሔር አንቺ የምትታመኝባቸውን ሁሉ ስላስወገድኩ ከእነርሱ የምታገኚው ምንም ነገር አይኖርም።”


በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፤ በቊጣውም ማዕበል ይደመሰሳሉ።


አማሌቃውያንና ከነዓናውያን በሸለቆዎቹ ውስጥ ስለሚኖሩ ነገ ተመልሳችሁ በቀይ ባሕር በኩል በሚወስደው መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።”


“እግዚአብሔር ግን ‘እኔ ከእናንተ ጋር ስለማልሆን ለመዋጋት አትውጡ፤ ይህ ካልሆነ ጠላቶቻችሁ ድል ይመቱአችኋል’ በላቸው አለኝ።


ታዲያ ስለምን ትእዛዙን አልፈጸምክም? ለምርኮስ በመሳሳትና በመስገብገብ እግዚአብሔርን ደስ የማያሰኝ ነገር ስለምን አደረግህ?”


Follow us:

Advertisements


Advertisements