Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 14:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ሙሴ እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ ለእስራኤላውያን በነገራቸው ጊዜ ምርር ብለው አለቀሱ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ሙሴም ይህን ለእስራኤላውያን ሁሉ በነገራቸው ጊዜ ክፉኛ ዐዘኑ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ሙሴም እነዚህን ቃላት ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ተናገረ፥ ሕዝቡም እጅግ አዘኑ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ሙሴም ይህን ነገር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ነገረ። ሕዝ​ቡም እጅግ አዘኑ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ሙሴም ይህን ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ነገረ፥ ሕዝቡም እጅግ አዘኑ።

See the chapter Copy




ዘኍል 14:39
8 Cross References  

ሰዎቹም ይህን የሚያሳዝን ቃል በሰሙ ጊዜ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ምንም ዐይነት ጌጣጌጥ ማድረግ አልፈለጉም።


በኋላም ዔሳው በረከትን እንደገና ለመቀበል በፈለገ ጊዜ ይህን በረከት እንደ ተከለከለ ታውቃላችሁ፤ እያለቀሰ እንኳ ያንን በረከት ተግቶ ቢፈልግ ሊያገኘው አልቻለም። ለንስሓ ምንም ዕድል አላገኘም።


የዚህ መንግሥት ወራሾች መሆን ይገባቸው የነበሩት ግን ውጪ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ። በዚያም ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”


አንድ ሰው በሞኝነቱ ጥፋት ሲደርስበት በእግዚአብሔር ላይ ያማርራል።


አምላክ ሆይ! በችግራቸው ጊዜ ፈለጉህ በገሠጽካቸውም ጊዜ በጸሎት ወደ አንተ ተመለሱ።


እነሆ! ይህን መልስ ስጣቸው፥ ‘በጠየቃችሁት ዐይነት እንደማደርግባችሁ ሕያው በሆነ ስሜ እምላለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤


ምድሪቱን ካጠኑት ሰዎች መካከል የተረፉት፥ የነዌ ልጅ ኢያሱና የይፉኔ ልጅ ካሌብ ብቻ ነበሩ።


እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን መቋቋም ያልቻሉበትም ምክንያት ይኸው ነው፤ እነርሱ ራሳቸው እንዲጠፉ ስለ ተፈረደባቸው ከጠላቶች ፊት ወደ ኋላ ይሸሻሉ። እንዲደመሰስ የታዘዘውን ነገር ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ እኔ ከእናንተ ጋር አልሆንም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements