Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 10:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ለሁለተኛ ጊዜ የማስጠንቀቂያውን ድምፅ ስታሰማ በስተደቡብ የሰፈሩት ሰፋሪዎች ጒዞ ይጀምሩ፤ በዚህም ዐይነት የማስጠንቀቂያ የመለከት ድምፅ የሚነፋው፥ ሰፈር ለቆ ጒዞ በሚጀመርበት ጊዜ ይሆናል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 መለከቱ ከፍ ባለ ድምፅ ለሁለተኛ ጊዜ ሲነፋ በስተ ደቡብ የሰፈሩት ነገዶች ጕዞ ይጀምሩ፤ ከፍ ያለው ድምፅ ጕዞ ለመጀመር ምልክት ይሆናል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ሁለተኛውንም የማስጠንቀቂያ መለከት ከፍ ባለ ድምፅ ስትነፉ በደቡብ በኩል የሰፈሩት ይጓዛሉ፤ የማስጠንቀቅያውን መለከት እንዲጓዙ ለመቀስቀስ ይነፋሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም በም​ል​ክቱ ስት​ነፉ በአ​ዜብ በኩል የሰ​ፈ​ሩት ይጓዙ፤ ሦስ​ተ​ኛ​ው​ንም በም​ል​ክቱ በነ​ፋ​ችሁ ጊዜ በባ​ሕር በኩል የሰ​ፈ​ሩት ይጓዙ፤ አራ​ተ​ኛ​ው​ንም በም​ል​ክቱ በነ​ፋ​ችሁ ጊዜ በመ​ስዕ በኩል የሰ​ፈ​ሩት ሠራ​ዊት ይጓዙ፤ ለማ​ስ​ጓዝ በም​ል​ክት ትነ​ፉ​ታ​ላ​ችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሁለተኛውንም ከፍ ባለ ድምፅ ስትነፉ በደቡብ በኩል የሰፈሩት ይጓዙ፤ ለማስጓዝ መለከትን ይነፋሉ።

See the chapter Copy




ዘኍል 10:6
3 Cross References  

ቀጥሎም በሮቤል ነገድ ቡድን ሰንደቅ ዓላማ ሥር የሚገኙት በሸዴኡር ልጅ በኤሊጹር መሪነት የቡድን ተራቸውን ጠብቀው ተጓዙ፤


ማኅበሩን በአንድነት እንዲሰበሰቡ ለማድረግ መለከት ትነፋለህ፤ ነገር ግን የማስጠንቀቂያውን ድምፅ አታሰማም፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements