ማቴዎስ 8:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 ኢየሱስ የገሊላን ባሕር ተሻግሮ፥ ወደ ጌርጌሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፥ አጋንንት የያዛቸው ሁለት ሰዎች ከመቃብር ቦታ ወጥተው ተገናኙት፤ በጣምም አደገኞች ስለ ነበሩ ማንም ሰው በዚያ መንገድ ማለፍ አይችልም ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም28 ባሕሩን ተሻግሮ ጌርጌሴኖን ወደሚባል አገር እንደ ደረሰ፣ አጋንንት ያደሩባቸው ሁለት ሰዎች ከሚኖሩበት የመቃብር ቦታ ወጥተው ተገናኙት። በዚያ መንገድ ሰው ማለፍ እስኪያቅተው ድረስ እጅግ አደገኞች ነበሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 ወደ ማዶ ወደ ጌርጋሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፥ አጋንንት ያደሩባቸው ሁለት ሰዎች ከመቃብር ስፍራ ወጥተው ወደ እርሱ መጡ፤ እነርሱም ሰው በዚያ መንገድ ማለፍ እስከማይችል ድረስ እጅግ አደገኞች ነበሩ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 ወደ ማዶም ወደ ጌርጋሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፥ አጋንንት ያደሩባቸው ሁለት ሰዎች ከመቃብር ወጥተው ተገናኙት፤ እነርሱም ሰው በዚያ መንገድ ማለፍ እስኪሳነው ድረስ እጅግ ክፉዎች ነበሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 ወደ ማዶም ወደ ጌርጋሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፥ አጋንንት ያደሩባቸው ሁለት ሰዎች ከመቃብር ወጥተው ተገናኙት፤ እነርሱም ሰው በዚያ መንገድ ማለፍ እስኪሳነው ድረስ እጅግ ክፉዎች ነበሩ። See the chapter |