Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 27:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በዚህ ምክንያት ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ “የደም መሬት” እየተባለ ይጠራል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስለዚህም ያ ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ “የደም መሬት” ተብሎ ይጠራል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በዚህም ምክንያት ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተብሎ ይጠራል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ “የደም መሬት” ተባለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ።

See the chapter Copy




ማቴዎስ 27:8
7 Cross References  

ይህም ነገር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ ታወቀ፤ ስለዚህ ያ መሬት በቋንቋቸው ‘አኬልዳማ’ ተብሎ ተጠራ፤ ትርጓሜውም ‘የደም መሬት’ ማለት ነው።


ስለዚህ ወታደሮቹ ገንዘቡን ተቀብለው ልክ እንደ ተነገራቸው አደረጉ፤ ይህም ነገር እስከ ዛሬ ድረስ በአይሁድ ዘንድ ተስፋፍቶ ይነገራል።


ያም ሰው ዘግይቶ ወደ ሒታውያን ምድር ሄዶ ከተማ ሠራና “ሎዛ” ብሎ ሰየማት፤ እስከ ዛሬም የምትጠራበት ስም ይኸው ነው።


ኢያሱም ደግሞ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው በቆሙበት በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ዐሥራ ሁለት የመታሰቢያ ድንጋዮችን አቆሙ፤ እነዚያም ድንጋዮች እስከ ዛሬ በዚያው ይገኛሉ፤


እግዚአብሔርም ከቤትፐዖር ከተማ ፊት ለፊት በሞአብ አገር በሚገኘው ሸለቆ ቀበረው፤ ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ እርሱ የተቀበረበትን ትክክለኛ ቦታ ለይቶ የሚያውቅ የለም።


መሎጊያዎቹ እጅግ ረጃጅሞች ስለ ነበሩ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት የቆመ ማንኛውም ሰው ሊያያቸው ይችላል፤ በሌላ አቅጣጫ የቆመ ግን ፈጽሞ ሊያያቸው አይችልም ነበር፤ እነዚህ መሎጊያዎች እስከ ዛሬ ድረስ በዚያው ይገኛሉ፤


ስለዚህ ከተመካከሩ በኋላ ለእንግዶች የመቃብር ቦታ እንዲሆን የሸክላ ሠሪውን መሬት ገዙበት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements