Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 27:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በዚያን ጊዜ ጲላጦስ በርባንን ፈቶ ለቀቀላቸው፤ ኢየሱስን ግን ካስገረፈው በኋላ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጣቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በዚህ ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ካስገረፈው በኋላ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠ።

See the chapter Copy




ማቴዎስ 27:26
11 Cross References  

እርሱ ግን ተወግቶ የቈሰለው ስለ መተላለፋችን ነው፤ የደቀቀውም ስለ በደላችን ነው፤ እኛ የዳንነው እርሱ በተቀበለው ቅጣት ነው፤ በእርሱም ቊስል እኛ ተፈወስን።


ከዚህ በኋላ ጲላጦስ ኢየሱስን ወስዶ አስገረፈው።


ጲላጦስ ሰዎቹን ደስ ለማሰኘት ብሎ በርባንን ፈቶ ለቀቀላቸው፤ ኢየሱስን ግን አስገረፈውና እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።


ስለዚህ ገርፌ እለቀዋለሁ።”


ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፥ ጢሜንም ለሚነጩ ጒንጬን ሰጠኋቸው፤ ከሚሰድቡኝና ከሚተፉብኝ ፊቴን አላዞርኩም።


ከኃጢአት ተለይተን በጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል።


አሕዛብም ያፌዙበታል፤ ይተፉበታል፤ ይገርፉታል፤ ይገድሉታልም፤ ነገር ግን ከሦስት ቀን በኋላ ይነሣል።”


ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል፤ እነርሱም ያላግጡበታል፤ ይገርፉታል፤ ይሰቅሉታልም፤ ግን በሦስተኛው ቀን ከሞት ይነሣል።”


በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲሰቀል ጲላጦስ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ኢየሱስን ይዘው ወሰዱት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements