Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 26:60 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

60 ብዙ የሐሰት ምስክሮች ቢቀርቡም፥ ሞት የሚያስፈርድበት ምስክርነት አላገኙም፤ በመጨረሻ ሁለት ምስክሮች ቀርበው፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

60 ብዙ የሐሰት ምስክሮች ቢቀርቡም በቂ ማስረጃ አላገኙም። በኋላ ግን ሁለት ሰዎች ቀርበው፣

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

60 ነገር ግን አላገኙም፤ብዙ የሐሰት ምስክሮች ቢመጡም ምንም አላገኙም፤ በመጨረሻም ሁለት መጥተው፥

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

60 ብዙም የሐሰት ምስክሮች ምንም ቢቀርቡ አላገኙም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

60 ብዙም የሐሰት ምስክሮች ምንም ቢቀርቡ አላገኙም።

See the chapter Copy




ማቴዎስ 26:60
7 Cross References  

“የአንድን ሰው ወንጀለኛነት ለማረጋገጥ አንድ ምስክር ብቻ አይበቃም፤ አንድ ሰው ወንጀለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ሁለት ወይም ሦስት ምስክሮች ያስፈልጋሉ።


ክፉ ሰዎች ባልሠራሁት ወንጀል ከሰሱኝ፤ በማላውቀውም ነገር በሐሰት መሰከሩብኝ።


የሐሰት ምስክሮች ዐመፅን እየተናገሩ በእኔ ላይ ስለ ተነሡ ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ።


መልሳችሁ ግን በገርነትና በአክብሮት ይሁን፤ የክርስቶስ በመሆናችሁ ባላችሁ መልካም ጠባይ ላይ ክፉ የሚናገሩ ሰዎች በክፉ ንግግራቸው እንዲያፍሩ መልካም ኅሊና ይኑራችሁ።


የማይነቀፍ ጤናማ ንግግርን ግለጥላቸው፤ በዚህ ዐይነት ተቃዋሚዎች በእኛ ላይ የሚናገሩት ክፉ ነገር ሲያጡ ያፍራሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements