Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 26:59 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

59 የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሸንጎ አባሎች ሁሉ በኢየሱስ ላይ የሞት ፍርድ ለማስፈረድ የሐሰት ምስክር ይፈልጉ ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

59 በዚህ ጊዜ የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሸንጎ በሙሉ ኢየሱስን ለማስገደል የሐሰት ማስረጃ ይፈልጉ ነበር፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

59 ሊቃነ ካህናትና ሸንጎው ሁሉ ሊገድሉት ፈልገው በኢየሱስ ላይ የሐሰት ምስክር ይፈልጉ ነበር፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

59 የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ሸንጎውም ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ የሐሰት ምስክር ይፈልጉ ነበር፤ አላገኙም፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

59 የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ሸንጕኦውም ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ የሐሰት ምስክር ይፈልጉ ነበር፥ አላገኙም፤

See the chapter Copy




ማቴዎስ 26:59
12 Cross References  

እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በወንድሙ ላይ የሚቈጣ ሁሉ ይፈረድበታል፤ ደግሞም ወንድሙን፥ ‘አንተ የማትረባ!’ ብሎ የሚሳደብ በሸንጎ ይፈረድበታል፤ ‘ደደብ!’ ብሎ የሚሳደብ ሁሉ በገሃነመ እሳት ይፈረድበታል።


በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሰክር ሰው የሰይፍ፥ የዱላና የተሳለ ፍላጻ ያኽል ሊጐዳው ይችላል።


የሐሰት ምስክሮች ዐመፅን እየተናገሩ በእኔ ላይ ስለ ተነሡ ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ።


በዚያን ጊዜ የካህናት አለቃው ኢየሱስን ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ ትምህርቱ ጠየቀው።


ታዲያ፥ ስለምን እኔን ትጠይቀኛለህ? ስናገራቸው የሰሙኝን ጠይቃቸው፤ የተናገርኩትን እነርሱ ያውቃሉ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements