Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 22:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ታዲያ፥ ዳዊት በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርቶ በተናገረ ጊዜ እንዴት ‘ጌታ’ ብሎ ጠራው?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ታዲያ፣ ዳዊት በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ለምን ‘ጌታዬ’ ይለዋል? ለምንስ፣ እንዲህ ይለዋል?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 እርሱም እንዲህ አላቸው፥ ታዲያ ዳዊት በመንፈስ ተመርቶ እንዴት ጌታ ብሎ ጠራው እንዲህ ሲል፦

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43-44 እርሱም “እንኪያስ ዳዊት ‘ጌታ ጌታዬን “ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፤” አለው፤’ ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43-44 እርሱም፦ እንኪያስ ዳዊት፦ ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል?

See the chapter Copy




ማቴዎስ 22:43
10 Cross References  

የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ አማካይነት ይናገራል፤ ቃሉም በአንደበቴ ነው።


ወዲያውኑ በመንፈስ ተመሰጥሁ፤ እነሆ በሰማይ ዙፋን አየሁ፤ በዙፋኑም ላይ አንድ አካል ተቀምጦበት ነበር።


በጌታ ቀን በመንፈስ ተመስጦ ላይ ሳለሁ የእምቢልታ ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ከበስተኋላዬ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤


ማንኛውም ትንቢት በሰው ፈቃድ ከቶ አልመጣም፤ ነገር ግን ትንቢት በመንፈስ ቅዱስ የተመሩ ሰዎች ከእግዚአብሔር ተቀብለው የተናገሩት ነው።


ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚለው “ዛሬ ድምፁን ስትሰሙ


“ወንድሞች ሆይ፥ ኢየሱስን ለያዙት ሰዎች መሪ ስለ ሆናቸው ስለ ይሁዳ፥ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል መፈጸም ነበረበት።


ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ፥ ‘እግዚአብሔር ለጌታዬ (ለመሲሑ)፥ ጠላቶችህን በእግርህ ሥር እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፤’ ብሎታል።


ስለዚህ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርቶ ኢየሱስን የሚረግም ማንም የለም፤ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ካልሆነ በቀር “ኢየሱስ ጌታ ነው!” የሚል ማንም እንደሌለ እነግራችኋለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements