Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 20:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 “እነሆ፥ አሁን ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳችን ነው፤ በዚያም የሰው ልጅ ለካህናት አለቆችና ለሕግ መምህራን ተላልፎ ይሰጣል፤ እነርሱም የሞት ፍርድ ይፈርዱበታል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “እንግዲህ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ የሰው ልጅ ለካህናት አለቆችና ለጸሐፍት ዐልፎ ይሰጣል፤ እነርሱም የሞት ፍርድ ይፈርዱበታል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 “እነሆ ወደ ኢየሩሳሌም እየሄድን ነው፤ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች ተላልፎ ይሰጣል፤ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 “እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች ይሰጣል፤ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፥ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች ይሰጣል፤ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል፥

See the chapter Copy




ማቴዎስ 20:18
15 Cross References  

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ይላቸው ጀመር፦ “ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ አለብኝ፤ እዚያም ከሽማግሌዎች፥ ከካህናት አለቆችና ከሕግ መምህራን መከራ ይደርስብኛል፤ ይገድሉኛል፤ ግን በሦስተኛው ቀን እነሣለሁ።”


እርሱም ራሱ እግዚአብሔር አስቀድሞ ባቀደውና ባወቀው አሠራር መሠረት ለእናንተ ተላልፎ ተሰጠ፤ እናንተም በዐመፀኞች እጅ እንዲሰቀልና እንዲሞት አደረጋችሁት።


ጠዋት በማለዳ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች ሁሉ በኢየሱስ ላይ የሞት ፍርድ ለማስፈረድ ተማከሩ።


ታዲያ፥ ምን ይመስላችኋል?” እነርሱም “ሞት ይገባዋል!” ሲሉ መለሱ።


“ከሁለት ቀን በኋላ የፋሲካ በዓል እንደሚሆን ታውቃላችሁ፤ የሰው ልጅ ለመሰቀል ተላልፎ ይሰጣል።”


እነርሱም “እንግዲህ ምን ምስክር ያስፈልገናል? እነሆ፥ ከአፉ የወጣውን ቃል እኛ ራሳችን ሰምተናል!” አሉ።


ቀናኢው ስምዖን፥ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ። አንዱ አስተያየት፥ ከቦታ ወይም ከሀገር ጋር ሲያያይዘው ሌላው ወገን ደግሞ ይሁዳን ውሸታም ወይም አታላይ ብሎ ለመስደብ የተሰጠ ቅጽል ነው ይላል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements