Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 15:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “ደቀ መዛሙርትህ የሽማግሌዎችን ወግ ስለምን ያፈርሳሉ? እነሆ! ምግብ የሚበሉት እጃቸውን ሳይታጠቡ ነው!”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “ደቀ መዛሙርትህ የአባቶችን ወግ የሚተላለፉት ለምንድን ነው? ምግብ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡም” አሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “ደቀ መዛሙርትህ ለምን የሽማግሌዎችን ልማድ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና” አሉት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “ደቀ መዛሙርትህ ስለ ምን የሽማግሎችን ወግ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና፤” አሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ደቀ መዛሙርትህ ስለ ምን የሽማግሎችን ወግ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና አሉት።

See the chapter Copy




ማቴዎስ 15:2
10 Cross References  

ኢየሱስ ምሳ ከመብላቱ በፊት እጁን ስላልታጠበ ፈሪሳዊው ተደነቀ።


ከኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አንዳንዶቹ በሥርዓት ባልነጻ ማለት ባልታጠበ እጅ እንጀራ ሲበሉ አዩአቸው።


በክርስቶስ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በሰው ሠራሽ ወግና በዓለማዊ ተራ ሥርዓት ላይ በተመሠረተ በፍልስፍናና በከንቱ ሽንገላ ማንም እንዳያጠምዳችሁ ተጠንቀቁ።


እናንተ ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ አኗኗር የተዋጃችሁት ጠፊ በሆነ በብር ወይም በወርቅ አለመሆኑን ታውቃላችሁ።


ስለዚህ ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን፥ “ደቀ መዛሙርትህ የሽማግሌዎችን ወግ በመጣስ፥ ስለምን እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ ይበላሉ?” ሲሉ ኢየሱስን ጠየቁት።


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ቀንን ከሌሊት ለመለየት ልዩ ልዩ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ላይ ይሁኑ፤ ለዕለታት፥ ለክፍላተ ዓመትና ለዓመታት መለያ ምልክት ይሁኑ፤


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እናንተስ ወጋችሁን ለመጠበቅ ብላችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለምን ታፈርሳላችሁ?


የአይሁድን እምነት በመጠበቅ በዘመኔ ከነበሩት ከብዙዎቹ አይሁድ ወገኖቼ ሁሉ እበልጥ ነበር፤ ስለ አባቶችም ወግ ከፍተኛ ቅናት ነበረኝ።


በቤተ መንግሥት ሥራ ላይ የተመደቡ ሌሎች ባለሥልጣኖች መርዶክዮስን “የንጉሡን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋለህ?” እያሉ፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements