Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 12:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 በዚያን ጊዜ አንዳንድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ኢየሱስን፥ “መምህር ሆይ! አንተ ተአምር ስታደርግ ማየት እንፈልጋለን!” አሉት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ከዚያም አንዳንድ ፈሪሳውያንና የአይሁድ ሃይማኖት መምህራን፣ “መምህር ሆይ፤ ከአንተ ምልክት ማየት እንፈልጋለን” አሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 በዚያን ጊዜ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ መለሱና “መምህር ሆይ! ከአንተ ምልክት ማየት እንፈልጋለን” አሉት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 በዚያን ጊዜ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ መለሱና “መምህር ሆይ! ከአንተ ምልክት እንድናይ እንወዳለን፤” አሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 በዚያን ጊዜ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ መለሱና፦ መምህር ሆይ፥ ከአንተ ምልክት እንድናይ እንወዳለን አሉ።

See the chapter Copy




ማቴዎስ 12:38
9 Cross References  

መቼም አይሁድ ተአምር ማየትን ይፈልጋሉ፤ የግሪክ ሰዎች ደግሞ ጥበብን ይሻሉ።


ከዚህ በኋላ የአይሁድ ባለሥልጣኖች ኢየሱስን፦ “አንተ ይህን ለማድረግ ሥልጣን እንዳለህ ምን ተአምር ታሳየናለህ?” አሉት።


ሌሎች ደግሞ ሊፈትኑት ፈልገው ከሰማይ አንድ ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁት።


ኢየሱስም “እናንተ ተአምራትና ድንቅ ነገር ካላያችሁ በቀር ምንም አታምኑም!” አለው።


ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ መጥተው በተሰበሰቡ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ይህ ትውልድ ክፉ ትውልድ ነው፤ ምልክት ለማየት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም።


እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “እኛ አይተን በአንተ እንድናምን ምን ተአምር ታደርጋለህ? ምንስ ትሠራለህ?


ከቃልህ የተነሣ ይፈረድልሃል፤ ከቃልህም የተነሣ ይፈረድብሃል።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements