Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 1:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ይሁን እንጂ፥ ልጅዋን እስከ ወለደች ድረስ አላወቃትም ስሙንም ኢየሱስ ብሎ ጠራው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ይሁን እንጂ የበኵር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም፣ “ኢየሱስ” ብሎ ጠራው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።

See the chapter Copy




ማቴዎስ 1:25
10 Cross References  

ከስምንት ቀን በኋላ ሕፃኑ በሚገረዝበት ሥነ ሥርዓት ላይ፥ ስሙ “ኢየሱስ” ተብሎ ተጠራ። ይህም ገና ከመፀነሱ በፊት መልአኩ ያወጣለት ስም ነው።


በዚያም የበኲር ልጅዋን ወለደች፤ በመታቀፊያ ጨርቅ ጠቀለለችው፤ በእንግዶች ማደሪያ ስፍራ ስላላገኙ በበረት በከብቶች መመገቢያ ግርግም ውስጥ አስተኛችው።


እርስዋ ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ስለሚያድን ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።”


“የእህልህን፥ የወይን ጠጅህንና የወይራ ዘይትህን በኲራት ለእኔ አቅርብ፤ “በኲር ሆነው የተወለዱትን ወንዶች ልጆችህን ለእኔ አቅርብ።


“ከእስራኤል ሕዝብም ሆነ ከእንስሶቹ በኲር ሆኖ የተወለደ ሁሉ ለእኔ መሆን ይገባዋል፤ ስለዚህ በኲር ሆኖ የተወለደውን ሁሉ ለእኔ እንዲሆን ቀድሰው።”


ይህም የሆነበት ምክንያት አስቀድሞ ያወቃቸው ልጁን እንዲመስሉና ልጁም ከብዙ ወንድሞች መካከል በኵር እንዲሆን እግዚአብሔር አስቀድሞ ስለ ወሰነ ነው።


ዮሴፍ ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ፥ የጌታ መልአክ ባዘዘው መሠረት እጮኛውን ማርያምን ወደ ቤቱ ወሰዳት።


እነሆ! ትፀንሺአለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።


ከዚህም የተነሣ የሳኦል ልጅ ሜልኮል እስከ ሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለደችም።


እርስዋም እጅግ ውብ ነበረች፤ ከንጉሡም ጋር ሆና በማገልገል ትንከባከበው ነበር፤ ይሁን እንጂ እርሱ ከእርስዋ ጋር አልተገናኘም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements