Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 15:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ጲላጦስም “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም “አንተ እንዳልከው ነው፤” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ጲላጦስም፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ሲል ጠየቀው፤ ኢየሱስም፣ “አንተው አልኸው፣” በማለት መለሰለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ጲላጦስም፥ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ሲል ጠየቀው፤ ኢየሱስም፥ “አንተው አልኸው፥” በማለት መለሰለት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ጲላጦስም “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም “አንተ አልህ፤” ብሎ መለሰለት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ጲላጦስም፦ አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን? ብሎ ጠየቀው። እርሱም፦ አንተ አልህ ብሎ መለሰለት።

See the chapter Copy




ማርቆስ 15:2
11 Cross References  

እንዲህም እያሉ ጠየቁ፦ “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ የት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ለእርሱ ልንሰግድለት መጥተናል።”


ለሁሉ ነገር ሕይወት በሚሰጠው በእግዚአብሔርና በጴንጤናዊው ጲላጦስ ፊት በመልካም መታመን በመሰከረው በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አዝሃለሁ።


ወንጀሉንም ለማመልከት “የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ጽሑፍ ተጽፎ ነበር።


“የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን!” እያሉ በማፌዝ እጅ ይነሡት ነበር።


ጲላጦስም፦ “ታዲያ፥ ይህን የአይሁድ ንጉሥ የምትሉትን ምን ላድርገው?” ሲል ሰዎቹን እንደገና ጠየቀ።


እርሱም “የአይሁድን ንጉሥ ፈትቼ እንድለቅላችሁ ትፈልጋላችሁን?” ሲል ጠየቃቸው።


የካህናት አለቆች ግን ኢየሱስን በብዙ ይወነጅሉት ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements