Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 11:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ማንም ሰው ‘ለምን ይህን ታደርጋላችሁ?’ ቢላችሁ፥ ‘ጌታ ስለሚያስፈልገው ነው፤ ወዲያውኑ መልሶ ይልከዋል፤’ በሉት።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ማንም፣ ‘ምን ማድረጋችሁ ነው?’ ቢላችሁ፣ ‘ለጌታ ያስፈልገዋል፤ እርሱም ወዲያውኑ መልሶ ይልከዋል’ በሉት።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ማንም፥ “ምን ማድረጋችሁ ነው?” ቢላችሁ፥ “ለጌታ ያስፈልገዋል፤ በቶሎም መልሶ ይልከዋል” ብላችሁ ንገሩት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ማንም ‘ስለ ምን እንዲህ ታደርጋላችሁ?’ ቢላችሁ ‘ለጌታ ያስፈልገዋል፤’ በሉት፤ ወዲያውም ደግሞ ወደዚህ ይሰደዋል፤” አላቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ማንም፦ ስለ ምን እንዲህ ታደርጋላችሁ? ቢላችሁ፦ ለጌታ ያስፈልገዋል በሉት፥ ወዲያውም ደግሞ ወደዚህ ይሰደዋል አላቸው።

See the chapter Copy




ማርቆስ 11:3
11 Cross References  

እናንተ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁ፤ እርሱ ምንም እንኳ ሀብታም ቢሆን በእርሱ ድኻ መሆን እናንተ ሀብታሞች እንድትሆኑ ስለ እናንተ ብሎ ድኻ ሆነ።


ሕይወትንና እስትንፋስን፥ ሌሎችንም ነገሮች ለሰው ሁሉ የሚሰጥ እርሱ ስለ ሆነ ምንም ነገር አይጐድለውም፤ የሰውም ርዳታ አያስፈልገውም።


እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ቃሉን መላኩ የታወቀ ነው፤ በሁሉ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰላምን እየሰበከ የመጣውም ለእነርሱ ነው።


እንዲህ ሲሉም ጸለዩ፦ “የሰውን ሁሉ ልብ የምታውቅ ጌታ ሆይ፥ ከነዚህ ከሁለቱ ማንን እንደ መረጥክ አሳየን፤


እርሱም በሰገነት ላይ ያለውን የተዘጋጀውንና የተነጠፈውን ትልቅ አዳራሽ ያሳያችኋል፤ በዚያ አዘጋጁልን።”


መግዛት በምትጀምርበት ቀን ሕዝብህ ይገዙልሃል፤ የተቀደሰውን መጐናጸፊያ ደርበህ ከአጥቢያ ኮከብ በፊት እንደ ጠል ወለድኩህ።


ምድርና በምድር ላይ የሚኖሩ ሁሉ፥ የእግዚአብሔር ናቸው፤ ዓለምና በውስጥዋ ያሉት ሁሉ የእርሱ ናቸው።


“በፊታችሁ ወዳለው መንደር ቀድማችሁ ሂዱ፤ እዚያም እንደ ደረሳችሁ ወዲያውኑ ማንም ሰው ገና ያልተቀመጠበት የአህያ ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፍቱትና ወዲህ አምጡት።


እነርሱም ሄደው ውርንጫውን በመንገድ ዳር በቤት ደጃፍ ታስሮ አገኙትና ፈቱት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements