Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 1:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እንዲህም ይል ነበር፦ “የጫማውን ማሰሪያ ጐንበስ ብዬ ለመፍታት እንኳ የማልበቃ ከእኔ እጅግ የሚበልጥ ከእኔ በኋላ ይመጣል፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስብከቱም፣ “እኔ ጐንበስ ብዬ የጫማውን ማሰሪያ መፍታት ከማይገባኝ፣ ከእኔ የሚበረታው ከእኔ በኋላ ይመጣል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስብከቱም፥ “እኔ ጐንበስ ብዬ የጫማውን ማሰሪያ መፍታት ከማይገባኝ፥ ከእኔ የሚበልጥ ከእኔ በኋላ ይመጣል፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል።

See the chapter Copy




ማርቆስ 1:7
11 Cross References  

ዮሐንስ ሥራውን በጨረሰ ጊዜ ‘እኔ ማን መሰልኳችሁ? እኔ መሲሕ አይደለሁም፤ ነገር ግን የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የማልበቃ ከእኔ በኋላ ሌላ ይመጣል’ ይል ነበር።


እርሱ ከእኔ በኋላ የሚመጣ ነው፤ እኔ የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የበቃሁ አይደለሁም።”


ዮሐንስ ግን ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ “እኔ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን ሌላ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል፤ እኔ የእርሱን ጫማ ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የበቃሁ አይደለሁም፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።


እነሆ፥ እኔ ለንስሓ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤ እርሱ ከእኔ እጅግ ይበልጣል፤ እኔ የእግሩን ጫማ እንኳ ለመሸከም የተገባሁ አይደለሁም።


ዮሐንስም “ይህስ አይሆንም፤ እኔ በአንተ እጅ መጠመቅ ሲገባኝ፥ እንዴት አንተ ወደ እኔ ትመጣለህ!” ብሎ ይከለክለው ጀመር።


አቢጌልም ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ በመንሣት “እኔ ለእርሱ ገረዱ ነኝ፤ የአገልጋዮቹንም እግር ለማጠብ ዝግጁ ነኝ” አለች።


የዮሐንስ ልብስ ከግመል ጠጒር የተሠራ ነበር፤ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የጣዝማ ማር. ነበር።


እኔ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል።”


ጳውሎስም “የዮሐንስ ጥምቀትማ ንስሓ ስለ መግባት የተፈጸመ ነው፤ ለሕዝቡም የተናገረው ‘ከእኔ በኋላ በሚመጣው እመኑ’ እያለ ነበር፤ እርሱም ኢየሱስ ነው” አላቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements