Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 1:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 በቤት ውስጥ፥ የስምዖን ዐማት በንዳድ ሕመም አተኲሶአት ተኝታ ነበር፤ ስለ እርስዋም መታመም ወዲያው ለኢየሱስ ነገሩት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 የስምዖን ዐማት በትኵሳት በሽታ ታምማ ተኝታ ነበር፤ ስለ እርሷም ነገሩት፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 የስምዖን አማት በትኩሳት በሽታ ታማ ተኝታ ነበር፤ ስለ እርሷም ነገሩት፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 የስምዖንም አማት በንዳድ ታማ ተኝታ ነበር፤ ስለ እርስዋም ወዲያው ነገሩት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 የስምዖንም አማት በንዳድ ታማ ተኝታ ነበር፥ ስለ እርስዋም ወዲያው ነገሩት።

See the chapter Copy




ማርቆስ 1:30
7 Cross References  

እንደ ሌሎች ሐዋርያትና እንደ ጌታ ወንድሞች እንደ ጴጥሮስም ክርስቲያን ሚስት አስከትለን የመዘዋወር መብት የለንምን?


እኅትማማቾቹም “ጌታ ሆይ፥ ያ የምትወደው ታሞአል” ብለው ወደ ኢየሱስ ላኩበት።


“ትንሽዋ ልጄ በሞት አፋፍ ላይ ናት፤ እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር እባክህ መጥተህ እጅህን ጫንባት!” ሲል አጥብቆ ለመነው።


ከዚያ ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ቤት በገባ ጊዜ የጴጥሮስ ዐማት አተኲሶአት ታማ እንደ ተኛች አየ።


በዚያኑ ጊዜ ኢየሱስ ከምኲራብ ወጥቶ ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ ስምዖንና እንድርያስ ቤት ገባ።


ኢየሱስም ወደ እርስዋ ቀረበና እጅዋን ይዞ አስነሣት፤ ትኲሳቱም ወዲያው ለቀቃት፤ ተነሥታም አስተናገደቻቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements