Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 9:61 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

61 አንድ ሌላ ሰው ደግሞ “ጌታ ሆይ፥ እኔ ልከተልህ እፈልጋለሁ፤ ነገር ግን መጀመሪያ ሄጄ ቤተሰቤን እንድሰናበት ፍቀድልኝ፤” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

61 ሌላ ሰው ደግሞ፣ “ጌታ ሆይ፤ መከተልስ እከተልሃለሁ፤ ነገር ግን ልመለስና መጀመሪያ የቤቴን ሰዎች እንድሰናበት ፍቀድልኝ” አለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

61 እንዲሁም ሌላው፦ “ጌታ ሆይ! እከተልሃለሁ፤ ነገር ግን መጀመሪያ ሄጄ በቤቴ ያሉትን እንድሰናበት ፍቀድልኝ፥” አለ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

61 ሦስ​ተ​ኛ​ውም፥ “አቤቱ፥ ልከ​ተ​ል​ህን? ነገር ግን ሄጄ ቤተ ሰቦ​ችን ሁሉ እን​ድ​ሰ​ና​በት ፍቀ​ድ​ልኝ” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

61 ደግሞ ሌላው፦ ጌታ ሆይ እከተልሃለሁ፤ ነገር ግን አስቀድሜ ከቤቴ ሰዎች እንድሰናበት ፍቀድልኝ አለ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 9:61
7 Cross References  

“ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሕይወት እንኳ ከእኔ አብልጦ የሚወድ ከሆነ የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም።


በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በሬዎቹን ትቶ ወደ ኤልያስ በመሮጥ “አባትና እናቴን ስሜ እንድሰናበት ፍቀድልኝ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ” አለው። ኤልያስም “እሺ፥ ተመልሰህ ሂድ፤ እኔ አልከለክልህም!” ሲል መለሰለት።


እነርሱ ለአንተ ሲሉ ወላጆቻቸውን ረስተዋል፤ ከዘመዶቻቸው ተለይተዋል፤ ልጆቻቸውን ትተዋል፤ ቃልህን አክብረዋል። ቃል ኪዳንህንም ጠብቀዋል፤


ባለህ ኀይል ሥራህን ሁሉ በትጋት ፈጽም፤ ወደ ሙታን ዓለም ከወረድህ በኋላ በዚያ ሥራና ሐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ የለም።


ነገር ግን ወንድሜን ቲቶን ባለማግኘቴ መንፈሴ አላረፈም፤ ስለዚህ እዚያ ያሉትን ክርስቲያኖች ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ ሄድኩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements