Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 9:42 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ልጁም ወደ ኢየሱስ በቀረበ ጊዜ ጋኔኑ በመሬት ላይ ጥሎ አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሠጸው፤ ልጁንም ፈውሶ ለአባቱ ሰጠው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ልጁ በመምጣት ላይ ሳለም ጋኔኑ መሬት ላይ ጥሎ አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሥጾ ልጁን ፈወሰው፤ ለአባቱም መልሶ ሰጠው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ልጁም በመምጣት ላይ ሳለ ጋኔኑ ጣለውና አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሥጾ ብላቴናውን ፈወሰው፤ ልጁንም ለአባቱ መልሶ ሰጠው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 ሲያ​መ​ጣ​ውም ጋኔኑ ጣለ​ውና አፈ​ራ​ገ​ጠው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን ክፉ ጋኔን ገሠ​ጸው፤ ልጁ​ንም አዳ​ነው፤ ለአ​ባ​ቱም ሰጠው። ሁሉም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ቅ​ነት የተ​ነሣ አደ​ነቁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ሲቀርብም ጋኔኑ ጣለውና አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኵሱን መንፈስ ገሥጾ ብላቴናውን ፈወሰው ለአባቱም መለሰው።

See the chapter Copy




ሉቃስ 9:42
12 Cross References  

የሞተው ቀና ብሎ ተቀመጠና መነጋገር ጀመረ፤ ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ለእናትዮዋ፥ “እነሆ፥ ልጅሽ፤” ብሎ ሰጣት፤


ስለዚህ ሰማያትና በውስጣቸው የምትኖሩ ሁሉ ደስ ይበላችሁ! ጥቂት ጊዜ ብቻ እንደ ቀረው ስላወቀ ዲያብሎስ በታላቅ ቊጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና ምድርና ባሕር ወዮላችሁ!”


እነሆ! ርኩስ መንፈስ በድንገት ይዞ ያስጮኸዋል፤ በመሬት ላይ ጥሎ ዐረፋ እያስደፈቀ ያንፈራግጠዋል፤ ሰውነቱንም እያቈሰለ በአሳር ይለቀዋል።


እነርሱም ልጁን ወደ እርሱ አመጡት፤ ርኩሱም መንፈስ ኢየሱስን ባየ ጊዜ ወዲያው ልጁን ጥሎ አንፈራገጠው፤ ልጁም በመሬት ላይ እየተንከባለለ ዐረፋ ይደፍቅ ጀመር።


ኤልሳዕም ግያዝን “ሱነማይቱን ጥራ” አለው፤ እርስዋም በመጣች ጊዜ ኤልሳዕ “ልጅሽ ይኸውልሽ!” አላት።


እርሱም እጁን ዘርግቶ ያዘና አስነሣት፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና ሌሎችንም አማኞች ጠርቶ ልጅቷን በሕይወት በፊታቸው አቀረባት።


ኤልያስ ልጁን ከሰገነት ወደ ምድር ቤት አውርዶ ለእናቱ በመስጠት “ተመልከቺ፤ እነሆ ልጅሽ ከሞት ወደ ሕይወት ተመልሶአል!” አላት።


ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “እናንተ እምነት የሌላችሁ ጠማማ ትውልድ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? እስቲ ልጅህን ወዲህ አምጣው።”


ሕዝቡም ሁሉ የእግዚአብሔርን ታላቅ ኀይል በማየታቸው ተገረሙ፤ ሁሉም ኢየሱስ ባደረገው ነገር በመደነቅ ላይ ሳሉ እርሱ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦


ደቀ መዛሙርቱ አምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ያኽል እየቀዘፉ ከተጓዙ በኋላ ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲቀርብ አይተው ፈሩ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements