Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 7:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ሴቶች ከወለዱአቸው ሰዎች መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 እላችኋለሁ፤ ከሴት ከተወለዱት መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ የለም፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም እላችኋለሁ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሴቶች ከወ​ለ​ዱ​አ​ቸው መካ​ከል ከመ​ጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ የሚ​በ​ልጥ ማንም አል​ተ​ነ​ሣም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ግን የሚ​ያ​ን​ሰው ይበ​ል​ጠ​ዋል።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።

See the chapter Copy




ሉቃስ 7:28
13 Cross References  

በእውነት እላችኋለሁ፤ ሴቶች ከወለዷቸው ሰዎች መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም። ነገር ግን በመንግሥተ ሰማያት በጣም የሚያንሰው ይበልጠዋል።


እርሱም “ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል ሁሉ የላከኝን ይቀበላል። ከእናንተ መካከል ከሁላችሁም የሚያንስ እርሱ ከሁሉ የሚበልጥ ይሆናል፤” አላቸው።


ዮሐንስ ግን ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ “እኔ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን ሌላ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል፤ እኔ የእርሱን ጫማ ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የበቃሁ አይደለሁም፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።


በዚያን ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ በረሓ እየሰበከ መጣ።


እርሱ ‘እነሆ! እፊት እፊትህ እየሄደ መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥’ ተብሎ የተጻፈለት ነው።


ይህን በሰሙ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቀራጮችም እንኳ ሳይቀሩ በዮሐንስ እጅ ተጠምቀው ስለ ነበር የእግዚአብሔር ሥራ ትክክል መሆኑን ተገነዘቡ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements