Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 6:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በሰንበት ቀን ኢየሱስ በእርሻ መካከል ሲያልፍ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ የስንዴ እሸት እየቀጠፉ በእጃቸው ማሸትና መብላት ጀመሩ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በአንድ የሰንበት ቀን ኢየሱስ በዕርሻ መካከል ያልፍ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱም እሸት ቀጥፈው በእጃቸው እያሹ ይበሉ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እነሆ፥ በሰንበት ቀን በእርሻ መካከል ሲያልፍ ሳለ ደቀመዛሙርቱ እሸት ቀጥፈው በእጃቸው እያሹ ይበሉ ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከዚ​ህም በኋላ ደግሞ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በሰ​ን​በት ቀን በእ​ርሻ መካ​ከል ሄደ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እሸት ቈር​ጠው በእ​ጃ​ቸው እያሹ በሉ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በሰንበትም በእርሻ መካከል ያልፍ ነበር ደቀ መዛሙርቱም እሸት ይቀጥፉ በእጃቸውም እያሹ ይበሉ ነበር።

See the chapter Copy




ሉቃስ 6:1
10 Cross References  

በአንድ ሰው የእህል ማሳ ውስጥ በምታልፍበትም ጊዜ እሸቱን በእጅህ እየቈረጥህ መብላት ትችላለህ፤ ነገር ግን ሰብሉን አጭደህ አትውሰድ።


ከእነዚህ ዕለቶች በመጀመሪያው ቀን ለአምልኮ ትሰበሰባላችሁ፤ ከዕለት ተግባራችሁ ማንኛውንም በዚህ ቀን አትሠሩም።


እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ሰባት ቀን ሙሉ እርሾ ያልነካውና ፈጽሞ ያልቦካ ቂጣ ብቻ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን እርሾውን ሁሉ ከየቤታችሁ ታስወግዳላችሁ፤ ማንም ሰው በነዚያ ሰባት ቀኖች እርሾ ያለበትን እንጀራ ቢበላ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ይወገዳል።


“የእህል አጨዳ ከጀመርክበት ጊዜ አንሥቶ ሰባት ሳምንት ቊጠር፤


“ነዶአችሁን ለእግዚአብሔር በመወዝወዝ የሚቀርብ ልዩ መባ አድርጋችሁ ካመጣችሁበት ሰንበት ማግስት ጀምሮ ሰባት ሳምንት ቊጠሩ፤


ብዙ ጊዜ የቈየ ደረቅ የወይን ጠጅ የጠጣ አዲሱን በተሐ የወይን ጠጅ መጠጣት አይፈልግም፤ ‘የቈየው ደረቅ የወይን ጠጅ የተሻለ ነው፥’ ይላልና።”


በሌላም ሰንበት ቀን ኢየሱስ ወደ ምኲራብ ገብቶ ያስተምር ነበር፤ እዚያም ቀኝ እጁ ሽባ የሆነ አንድ ሰው ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements