Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 4:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በምኲራቦቻቸውም ያስተምር ነበር፤ ሁሉም በትምህርቱ አመሰገኑት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እርሱም በምኵራባቸው ያስተምር ነበር፤ ሰውም ሁሉ ያመሰግነው ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እንዲሁም በሁሉም እየተመሰገነ በምኵራባቸው ያስተምር ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በየ​ም​ኵ​ራ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር፤ ትም​ህ​ር​ቱ​ንም ያደ​ንቁ ነበር፤ ሁሉም ያመ​ሰ​ግ​ኑት ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እርሱም በምኵራባቸው ያስተምር፥ ሁሉም ያመሰግኑት ነበር።

See the chapter Copy




ሉቃስ 4:15
10 Cross References  

ኢየሱስም በምኲራቦቻቸው እያስተማረና የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ፥ በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የተያዙትንም ሰዎች እየፈወሰ በገሊላ ምድር ሁሉ ይዘዋወር ነበር።


ሕዝቡም ይህን ባዩ ጊዜ ተገረሙ፤ እንዲህ ያለውንም ሥልጣን ለሰው በመስጠቱ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።


ኢየሱስ በሰንበት ቀን ከምኲራቦቹ በአንዱ ያስተምር ነበር፤


ይሁን እንጂ ሰውየው ከዚያ ወጥቶ ይህን ነገር ለሰው ሁሉ ማውራት ጀመረ። በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ወደ ማናቸውም ከተማ በግልጥ መግባት አልቻለም። ነገር ግን ከከተማ ውጪ ሰው በሌለበት ቦታ ይኖር ነበር፤ ሆኖም ሰዎች ከየስፍራው ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።


ስለዚህ በየምኲራቦቻቸው እያስተማረና አጋንንትን እያስወጣ በገሊላ ሁሉ ይዘዋወር ነበር።


“ይህ ምንድን ነው? ምን ዐይነት አዲስ ትምህርት ነው? ርኩሳን መናፍስትን እንኳ በሥልጣኑ ያዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታል፤” እያሉ ሁሉም በመገረም እርስ በርሳቸው ይጠያየቁ ጀመር።


ወደ አገሩ ወደ ናዝሬት ከተማ መጥቶ በምኲራቦቻቸው ሕዝብን ያስተምር ነበር፤ የሰሙትም ሁሉ በመደነቅ እንዲህ ይሉ ነበር፤ “ይህ ሰው ይህን ጥበብና ይህን ድንቅ ሥራ ከወዴት አመጣው?


ኢየሱስም በምኲራቦቻቸው እያስተማረ፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከ፥ ሕዝቡን ከበሽታና ከደዌ ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተሞችና በመንደሮች ሁሉ ይዘዋወር ነበር።


እኔ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክህ ስላከበርኩህ እነሆ፥ የማታውቃቸውን ሕዝቦች ትጠራለህ፤ የማያውቁህም ሕዝቦች ወደ አንተ ይፈጥናሉ።”


ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ወደ አደገበት አገር ወደ ናዝሬት ሄደ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኲራብ ገባ፤ ሊያነብም ተነሣ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements