Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 23:53 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

53 አስከሬኑንም አውርዶ በቀጭን ሐር ልብስ ከፈነው፤ ማንም ሰው ባልተቀበረበት ከአለት ተወቅሮ በተዘጋጀ መቃብር ውስጥ ቀበረው፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

53 በተፈቀደለትም ጊዜ፣ ሥጋውን አውርዶ በበፍታ ከፈነው፤ ከድንጋይ ተፈልፍሎ በተሠራና ገና ማንም ባልተቀበረበት መቃብር ውስጥ አስቀመጠው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

53 አውርዶም በቀጭን ሐር ልብስ ከፈነው፤ ማንም ገና ባልተቀበረበት ከዓለትም በተወቀረ መቃብር አኖረው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

53 ሥጋ​ው​ንም አው​ርዶ በበ​ፍታ ገነ​ዘው፤ ማንም ባል​ተ​ቀ​በ​ረ​በት፥ ከድ​ን​ጋ​ይም በተ​ፈ​ለ​ፈለ መቃ​ብር ቀበ​ረው፤ ታላቅ ድን​ጋ​ይም አን​ከ​ባ​ልሎ መቃ​ብ​ሩን ገጥሞ ሄደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

53 አውርዶም በተልባ እግር ልብስ ከፈነው፥ ማንም ገና ባልተቀበረበት ከዓለትም በተወቀረ መቃብር አኖረው።

See the chapter Copy




ሉቃስ 23:53
7 Cross References  

ዮሴፍ አዲስ የከፈን ልብስ ገዛና የኢየሱስን አስከሬን ከመስቀል አውርዶ ገነዘው፤ ከአለት ተወቅሮ በተዘጋጀ መቃብር ውስጥ ቀበረው። ትልቅ ድንጋይም አንከባሎ መቃብሩን ዘጋ።


ምንም ዐመፅ ሳይፈጽም፥ በአንደበቱም ሐሰት ሳይገኝበት፥ በሞቱ ከክፉ አድራጊዎች ጋር ተቈጠረ፤ በባለጸጋም መቃብር ተቀበረ።”


ይህ ሰው ወደ ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የኢየሱስ አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀ።


ይህንንም ያደረገው ዓርብ ማታ ለሰንበት ዝግጅት በሚደረግበት ጊዜ ነበር።


ኢየሱስ ተሰቅሎ በነበረበት ቦታ አንድ የአትክልት ስፍራ ነበረ፤ በዚያም የአትክልት ስፍራ ውስጥ ማንም ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበር።


ስለ እርሱ የተጻፈውን ሁሉ ከፈጸሙበት በኋላ ከመስቀል አውርደው ቀበሩት፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements