Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 23:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እነርሱ ግን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “ስቀለው!” እያሉ ጮኹ፤ የሕዝቡና የካህናት አለቆች ድምፅ አየለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እነርሱ ግን ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ እንዲሰቀል አጥብቀው ለመኑት፤ ጩኸታቸውም በረታ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እነርሱ ግን እንዲሰቀል በታላቅ ድምፅ አጥብቀው ለመኑት። የእነርሱ ጩኸትና የካህናት አለቆችም ድምፅ በረታ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እን​ዲ​ሰ​ቅ​ሉ​ትም ቃላ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው እየ​ጮሁ ለመኑ፤ ጩኸ​ታ​ቸ​ውና የካ​ህ​ናት አለ​ቆች ድም​ፅም በረታ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እነርሱ ግን እንዲሰቀል በታላቅ ድምፅ አጽንተው ለመኑት። የእነርሱ ጩኸትና የካህናት አለቆችም ቃል በረታ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 23:23
7 Cross References  

ሦስቱ እረኞች እኔን ስላስቈጡኝና ስለ ጠሉኝ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አስወገድኳቸው።


ጥርሶቻቸው እንደ ጦሮችና ቀስቶች፥ ምላሶቻቸው እንደ ተሳሉ ሰይፎች በሆኑ፥ ሰውን በሚበሉ አንበሶች መካከል ተደፍቼ ተኝቼአለሁ።


እነርሱ ግን “ይህ ሰው ከገሊላ ጀምሮ እስከዚህ ድረስ፥ በይሁዳ ምድር ሁሉ እያስተማረ ሕዝቡን ለሁከት ያነሣሣል” እያሉ በጥብቅ ከሰሱት።


ጴጥሮስ ግን “መሞት እንኳ ቢያስፈልግ ከአንተ ጋር እሞታለሁ እንጂ ከቶ አልክድህም!” እያለ አጠንክሮ ተናገረ። የቀሩትም ደቀ መዛሙርት እንዲሁ ይሉ ነበር።


ጲላጦስም ሦስተኛ ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ይህ ሰው ያደረገው በደል ከቶ ምንድን ነው? እኔ ለሞት የሚያደርስ ምንም ነገር አላገኘሁበትም፤ ስለዚህ ገርፌ እለቀዋለሁ።”


በዚህም ምክንያት የጠየቁት እንዲደረግላቸው ጲላጦስ ፈረደ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements