Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 22:55 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

55 ሰዎቹ በግቢው ውስጥ እሳት አቀጣጥለው በአንድነት ተቀምጠው ነበር። ጴጥሮስም መጥቶ አብሮ ተቀመጠ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

55 ሰዎቹ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ እሳት አንድደው በአንድነት ተቀምጠው ሳለ፣ ጴጥሮስም ከእነርሱ ጋራ ተቀምጦ ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

55 በግቢው መካከልም እሳት አንድደው፥ በአንድነት ተቀምጠው ሳሉ ጴጥሮስ በመካከላቸው ተቀመጠ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

55 በግ​ቢ​ውም ውስጥ እሳት አን​ድ​ደው ተቀ​መጡ፤ ጴጥ​ሮ​ስም አብ​ሮ​አ​ቸው በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተቀ​መጠ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

55 በግቢ መካከልም እሳት አንድደው በአንድነት ተቀምጠው ሳሉ ጴጥሮስ በመካከላቸው ተቀመጠ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 22:55
14 Cross References  

አትታለሉ፤ “መጥፎ ጓደኛ ጥሩውን ጠባይ ያበላሻል።”


ልቡም በጣም ተጨንቆ በብርቱ ይጸልይ ነበር፤ ላቡም እንደ ደም ሆኖ ወደ መሬት ይንጠባጠብ ነበር።


በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች በካህናት አለቃው ግቢ ተሰበሰቡ።


ከጥበበኞች የሚወዳጅ ጥበበኛ ይሆናል። ማስተዋል ከጐደላቸው ሰዎች ጋር ጓደኛ የሚሆን ግን ይጐዳል።


ዕውቀት ከጐደላቸው ሰዎች ተለይ! በሕይወትም ትኖራለህ፤ በማስተዋልም መንገድ ወደፊት ተራመድ።”


የክፋትን ሥራ ከሚሠሩ ክፉ ሰዎች ጋር አትውሰደኝ፤ እነርሱ ከጐረቤቶቻቸው ጋር በሰላም ይነጋገራሉ፤ በልባቸው ግን ተንኰል አለ።


በክፉ ሰዎች ምክር የማይሄድ፥ የኃጢአተኞችን መንገድ የማይከተል፥ ከፌዘኞች ጋር ኅብረት የማያደርግ የተባረከ ነው።


ጴጥሮስ በእሳቱ አጠገብ ተቀምጦ ሳለ አንዲት ገረድ በእሳቱ ብርሃን አየችው፤ ወደ እርሱ ትኲር ብላ ተመልክታም “ይህም ከኢየሱስ ጋር ነበር!” አለች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements